የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የህትመትና ማስታወቂያ ስራ እና ልዩ ልዩ ቋሚ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 21, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2017

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በግልጽ ጨረታ ቁጥር /// ግጨ/01/2017 . ሎት አንድ፣ የህትመትና ማስታወቂያ ስራ፣ሎት ሁለት፣ ልዩ ልዩ ቋሚ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  • የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (ቲን ነምበር) የአቅራቢነት ሰርተፍኬት፤ ከገቢዎችና ጉምርክ ባለስልጣን በጨረታ መሳተፍ ስለመቻላችሁ የሚገልጽ ማስረጃ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባችሁ፤
  • ማስታወቂያው አየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ሆኖ 11ኛው ቀን 400 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከረፋዱ 430 ሰዓት ይከፈታል
  • ተጫራቾች የቴከኒክና የዋጋ ፖስታቸውን ለይተው ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የቴክኒክ ፖስታው ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችና የጨረታ ማስከበሪያ መያዝ ያለበት ሆኖ በጨረታ መክፈቻ ወቅት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  • የጨረታ ሰነዱን ከአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ከመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 507 ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 800 ሰዓት በማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመግዛት መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት አንድ 10,000.00 ብር እና ሎት ሁለት 20,000 CPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች በሚሞሉት ሰነድ ላይ የድርጅታቸውን ማህተም እና ህጋዊ ውክልና ባለው አካል በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፊርማ ማድረግ እና መፈርም አለባቸው፡፡

ማሳሰቢያ፡/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡መገናኛ ስሪ ኤም ሞል ህንፃ 5 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 507

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011- 639-4655 / 011-639-3010 መጠየቅ ይቻላ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ