የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዱቄት ፋብሪካ ሕንጻ ከነ ዱቄት ፋብሪካ ማሽነሪዎቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል


Reporter(Sep 21, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የሐራጅ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/901147/2011 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል.

.

የተበዳሪ ስም

የንብረት አስያዥ ስም

ቅርንጫፍ

 

አድራሻ

 

የይዞታው ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር

የይዞታ ስፋት (ካ.ሜ)

የይዞታው አይነት/የሚሰጠው  አገልግሎት

የሐራጁ መነሻ ዋጋ (ብር)

 

ሀራጁ የሚከናወንበት ቀን እና ሰዓት

1

አቶ ዓለሙ ጆቢር ሁርሳ

ተበዳሪው

 

ዋልኬሳ

 

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን አሰላ ከተማ ጢዮ /ከተማቀበሌ 10

4055/279/91

2580

የዱቄት ፋብሪካ ሕንጻ ከነ ዱቄት ፋብሪካ ማሽነሪዎቹ

 

28,032,798.22

 

11/02/2018 .3:00-4:00

 

በመሆኑም፡

  1. ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4 በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላል:: የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ ማቅረብ ተመራጭ ነው።
  2. ጨረታዉ የሚከናወነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋናው መስሪያ ቤት 42 (ወለል) ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4203 ነው።
  3. የንግድ ማህበርን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻ እና መተዳደርያ ደንብ የያዘና በማህበሩ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል።
  4. የጨረታ አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል።
  5. ንብረቱን አሰላ ዲስትሪክት ህግ አገልግሎት በመቅረብ ወይም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት 42 ፎቅ በአካል በመቅረብ በሚመቻች ፕሮግራም መጎብኘት ይቻላል።
  6. በጨረታው ከፍተኛ የሆነ የጨረታ ዋጋ የሰጠ ተጫራች በባንኩ የጨረታ አሸናፊነት ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ቀሪ የሽያጩን ገንዘብ 15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጁ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
  7. ባንኩ ሐራጁን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111-13-05-08 በመደወል ወይም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋና /ቤት 42 ፎቅ ላይ በሚገኘው ሕግ ክፍል ወይም አሰላ ዲስትሪክት ሕግ አገልግሎት በአካል ቀርቦ ማነጋገር ይቻላል።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *