Your cart is currently empty!
ፀደይ ባንክ አ.ማ መኪና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Reporter(Sep 21, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
ፀደይ ባንክ አ.ማ ለአቶ ዉብሸት ጥላሁን ሀይሌ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን በሰንጠረዡ የተዘረዘውን መኪና በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና በተሸሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: በመሆኑም ተጫራጮች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራጮች የመኪናዉን የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በፀደይ ባንክ አማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማሲያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ::
- በጨረታው የሚሳተፈው በህግ ሰውነት ያገኘ ድርጅት ከሆነ ፣ የድርጅቱ መመስረቻ ጹሁፍ ወይም መተዳደሪያ ደንብ፣ህጋዊ ሰውነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ውክልና ማቅረብ አለበት::
- የጨረታ አሸናፊው አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ፀድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ይሆናል::
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል:: በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ የአሲያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል::
- በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራጮች ያሲያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል::
- የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚካፈሉ ክፍያዎች፤ ግብር፣ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ሚከፈል ከሆነ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጭዎች ይከፍላሉ::
- ተጫራጮች መኪናዉን በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ::
- የጨረታው የሚካሄደዉ ፀደይ ባንክ ዋናዉ መስራቤት 9ኛ ፎቅ ነው::
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0939115010 በመደወል መጠየቅ ይቻላል::
ተ.ቁ |
የተበዳሪ ስም |
የመያዣ ሰጪ ስም |
የተሽከርካሪዉ አይነት |
የሞተር ቁጥር |
የሻንሲ ቁጥር
|
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
የጨረታ ቀንና ሰዓት
|
ጨረታው የወጣው
|
|
1 |
አቶ ዉብሸት ጥላሁን
|
አቶ ዉብሸት ጥላሁን
|
የ2022 ስሪት CZF63S ሞዴ፣ በቤንዚን የሚሰራ፣ 4 ሰዉ የመጫን አቅም ያለዉ፣ 1200 ሲሲ፣ባለ 4 ሲሊንደር እና 82 የሞተር ፈረስ ጉልበት ያለዉ፣ ጃፓን ሱዚኪ ዲዛየር አዉቶሞቢል |
K12MP4 351306 |
MBHCZF6 3S00337105
|
2,363.961.60 (ሁለትሚሊየን ሶስት መቶ ሰልሳ ሶስት ሽህ ዘጠኝ መቶ ሰልሳ አንድ ብር ከ 60 ሳንቲም) |
መስከረም 27/2017 ዓ/ም
|
ከጥዋቱ 3፡00 ሰዓት-6፡00 ሰዓት |
ለሁለተኛ ጊዜ |