በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በ2018 በጀት በ1ኛ ሩብ ዓመት የምልምል ሰልጣኝ ወታደሮችና በሆስፒታል ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን ቀለብ የግብርና ምርት ውጤቶችን፣ የኢንዱስትሪ ምርቶችና የባልትና ውጤቶችን እንዲሁም የተጣራ የበሬ ስጋ እና የበቆሎ ቅንጬ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 23, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት 2018 በጀት 1 ሩብ ዓመት የምልምል ሰልጣኝ ወታደሮችና በሆስፒታል ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን ቀለብ በሎት 1 የግብርና ምርት ውጤቶችን፤ በሎት 2 የኢንዱስትሪ ምርቶችና የባልትና ውጤቶችን እንዲሁም በሎት 3 የተጣራ የበሬ ስጋ እና የበቆሎ ቅንጬ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ተጫራች ማሟላት የሚገባቸው

1. ተጫራች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያለው፣

2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤

4. የግብር ከፋይ ምዝገባ (ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችል፤

5. የዘመኑ ግብር የከፈለ /ከኢትዮ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን/ በጨረታ ለመሳተፍ የተሰጠው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤

6. በቀለብ አቅርቦት የመልካም ሥራ አፈፃፀም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።

7. ተወካይ ከሆነ /ከሆነች/ ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት።

8. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያው የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ ማድረግ ይኖርባቸዋል።

9. ተጫራች የአንድ ዋጋ መሞላት ያለበት ያለ ቫት ሆኖ ሁሉንም ቀለቦች ዋጋ በመሙላት ወደ ጎን አባዝቶ እና ወደ ታች ደምሮ ማስቀመጥ ይኖርበታል።

10. በጨረታ አሸናፊ የሚለየው በሎት 1 እና በሎት 2 ላይ በተቀመጠው የቀለብ ዝርዝር በጠቅላላ ድምር ዝቀተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች አሸናፊ ሆኖ ይመረጣል:: በሎት 3 በተቀመጠው ዝርዝር በተናጠል ዝቀተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች አሸናፊ ሆኖ ይመረጣል።

11. በሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም:: ስርዝ ድልዝ ካለ እና ከተጠቀሙ ሰነዱ ከውድድር ውጭ ይሆናል።

12. ተጫራቹ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ሲያቀርቡ ኦርጅናልና ኮፒ ብለው መለየት ይኖርባቸዋል፡፡ ኦርጅናሉን ፋይናንሻል ለብቻ በማሸግ ኮፒውን ፋይናንሻል ለብቻ በማሸግ እንዲሁም ከተራ ቁጥር 1-7 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በብቻው በአንድ ፖስታ በማሸግ በመጨረሻ ሶስቱንም ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግ የሚወዳደሩበትን ሎት በመፃፍ ማቅረብ አለበት፡፡ በዚህ መሰረት ሶስቱንም ፖስታዎች ለየብቻ ሳያሽግ በአንድ ላይ አሽጎ ቢመጣ ከውድድር ውጭ ይሆናል።

13. ተጫራች በጨረታ ማስከበሪያ ባቀረቡት ዋጋ ልክ 2% በጥሩ ገንዘብ ወይም በክፍያ ማዘዣ CPO ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት።

14. የጨረታ አሸናፊዎች ውል ማስከበሪያ ካሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ 10% በጥሬ ገንዘብ ወይም CPO ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት።

15. የጨረታ ሰነዱን ከማሰልጠኛ /ቤቱ ፋይናንስ ዴስክ በስራ ቀንና ሰዓት 13/01/2018 ዓም ጀምሮ እስከ 21/01/2018 . ድረስ የሚጫረቱበትን የመጫረቻ ሰነድ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

16. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን 22/01/2018 . ከጠዋቱ 200 እስከ 700 ሰዓት ድረስ በማ//ቤቱ ቢሮ በር ላይ በሚዘጋጀው ሳጥን ሰነዱን ማስገባት አለባቸው:: በዚሁ ቀን 23/01/2018 / ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማ//ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ከቀኑ 730 ሰዓት ላይ ጨረታው ይከፈታል።

17. አሸናፊ የሆነው ተጫራች //ቤቱ በየሳምንቱ፣ በየ 15 ቀኑ ወይም በየወሩ በሚሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ጥራቱን በጠበቀ መንገድ ቀለቡን አሟልቶ ማቅረብ የሚችል እና በማ//ቤቱ የጥራት ኮሚቴ ጥራቱን አረጋግጦ ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡ የቀለቡን ጥራት የጥራት ኮሚቴው ካልተቀበለው 3-5 ባሉት ቀናት ውስጥ ቀይሮ ጥራት ያለው ቀለብ የማቅረብ ግዴታ አለበት።

18. አሸናፊ የሆነው ነጋዴ ለቀለብ አቅርቦት ክፍያ በሚጠይቅበት ጊዜ ህጋዊ ደረሰኝ ከካሽ ሬጅስተር ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት።

19. የቀለብ አቅርቦት የውል ስምምነቱ ከተፈፀመበት ቀን ጀምሮ 5-6 ወራት ድረስ //ቤቱ በሚሰጠው የቀለብ ማዘዣ መሰረት እየቀረበ የጨረታ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡ የዋጋ ማሻሻያም አይደረግበትም።

20. //ቤቱ በጀቱን በማረጋገጥ 20% የመቀነስም ሆነ 20% የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።

21. //ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

22. በዚህ ማስታወቂያ ያልተገለፁ ሌሎች ህጎች በሀገሪቱ የግዥ አፈፃፀም መምሪያ መሠረት ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል።

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 760 0018 በስራ ሰዓት ደውሎ ማረጋገጥ ይችላሉ።

የብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና //ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *