በልደታ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የጅምናዝየም ዕቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 22, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር SM 01/2018

በልደታ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን በግልፅ ጨረታ ቁጥር SM01/2018 ዓ.ም ከዚህ በታች ለተዘረዘሩትን የጅምናዝየም ዕቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ሎት 1 የስፖርት ጅምናዝየም ዕቃዎች ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00

1. ተጫራቾ የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በልደታ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን በመቅረብ  ለእያንዳንዱ ጥቅል የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

2. ተጫራቾች፡-

ሀ. በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው

ለ. የተጨማሪ እሴት ታስክ የተመዘገበ ፣ታክስ ክሊራንስ እና ቲን ነበር ማቅረብ የሚችል።

3. በየሎቱ በተቀመጠው መሠረት የጨረታ ማስከበርያ የብር መጠን (CPO) የልደታ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት” በሚል ስም በማሰራት ከሰነዱ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ውስጥ በሚገኘው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ የተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በልደታ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

5. ለጨረታ ከቀረቡት አገልግሎቶች ዝርዝር ውስጥ ጽ/ቤቱ 25 ጨምሮም ሆነ ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።

6. ተጫራቾች በጨረታው ቢያሸንፉ ሊያቀርቡ የሚችሉትን አገልግሎቶች ናሙና ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን፣ በጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ ተገልፆ በሚሰጠው የግዥ ትዕዛዝ መሠረት አገልግሎቶችን ቀደም ሲል አቅርቦት በተመረጠው ናሙና መሠርት ለመ/ቤታችን ለማቅረብ አለበት።

7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በመጨረሻው ቀን ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

8. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ- በልደታ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር 0118722106 አዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ መሬት አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አጠገብ ወይም በላይ ተክሉ ኬክ ቤት አጠገብ 5ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502

በልደታ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *