Your cart is currently empty!
በድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጽ/ቤት በ2018ዓ.ም በጀት ዓመት ለአስተዳደሩ መ/ቤቶች፣ ቢሮዎች፣ ጽ/ቤቶች እና ቀበሌዎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የጤና ባለሙያዎች ጫማ፣ የድጋፍ ሰጪ ጫማ እና የስራ መሳሪያዎችን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያውን አውጥቶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨ/መ/ቁ ግዥ/ን/ማ 512/የመ/ግ/ጨ/004/2018
በድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጽ/ቤት በ2018ዓ.ም በጀት ዓመት ለአስተዳደሩ መ/ቤቶች፤ ቢሮዎች፤ ጽ/ቤቶች እና ቀበሌዎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የጤና ባለሙያዎች ጫማ፤ የድጋፍ ሰጪ ጫማ እና የስራ መሳሪያዎችን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያውን አውጥቶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዙሁ መሰረት፡–
1/ በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
2/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3/ በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።
4/ ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የጨረታ ሠነዱን ከመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 204 ቀርበው ለእያንዳንድ ሎት ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል መግዛት የሚችሉ ሲሆን በጨረታ መክፈቻው እለት የጨረታ ሠነዱን በትክክል ሞልተው ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዋናውንና ኮፒውን በአግባቡ አሽገው ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
5/ የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ላይ ታሽጎ በዛው ዕለት 4፡30 ላይ ተጫራቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 215 በግልጽ ሲከፈት፤ ቀኑ በዓል ወይም የዕረፍት ቀናት ላይ ከዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።
6/ ተጫራቶች ለእያንዳንዱ ሎት ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይንም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7/ መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8/ ተጨማሪ ማብራሪያና መረጃ ቢያስፈልግ በሚከተለው አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡–
በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጽ/ቤት
ቢሮ ቁጥር 215
የስልክ ቁጥር 0915-75-57-68 / 0254-11-01-79 ፋክስ ቁጥር 0254-11-01-79
ድሬዳዋ
በድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ