Your cart is currently empty!
የሀረሪ መንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የፈርኒቸር እቃዎች ግዥ እና የኤሌከትሮኒክስ እቃዎች ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀረሪ መንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ሰጪ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት አመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የግዥ/መ/ቁ |
የእቃው አይነት መገለጫ |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን በብር |
ብዛት |
|
1 |
PPPDSO/001/18 |
የፈርኒቸር እቃዎች ግዥ |
150,000.00 |
10 የተለያዩ አይነቶች ብዛታቸው 308 |
|
2 |
PPPDSO/002/18 |
የኤሌከትሮኒክስ እቃዎች ግዥ |
150,000.00 |
26 የተለያዩ አይነቶች ብዛታቸው 88 |
1. የብቃት መስፈርቶች፡– ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ የተጠየቁ ህጋዊነትን የሚያመለከቱ ሰነዶች ቅጂ እና ሌሎች በጨረታ ሰነዱ የተጠየቁ ከስራው ጋር የተያያዙ ሰነዶችን ከጨረታው መልስ ጋር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው፡–ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለ60 ቀናት ይሆናል።
3. የጨረታ ማስከበሪያ፡– ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ (ጥሬ ገንዘብ ከፍያ ማዘዣ) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና በመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት ስም ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
4. የጨረታ ሰነድ ግዥና ቋንቋ፡– የጨረታ ሰነዱ የተዘጋጀው በአማርኛ ቋንቋ ነው፡፡ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች በጽ/ቤቱ ግዥ ፋይናንስና ንበረት ስራ ከፍል ለግዥ መለያ ቁጥር PPPDSO/001/2018 እና PPPDSO/002/2018 የማይመለስ 500 (አምስት መቶ/ ብር በመክፈል ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
5. የጨረታው አቀራረብ እና አይነት፡–
5.1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዳቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
5.2. የጨረታው ዓይነት ባለአንድ ኤንቨሎፕ ሲሆን ተጫራቾች ቴከኒካልና ፋይናንሽያል ስነዶቻቸውን በጨረታ መመሪያው መሠረት በማያያዝ ለእያንዳንዳቸው አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
6. የጨረታ መክፈቻና መዝጊያ ቀን፡– የግዥ መለያ ቁጥር PPPDSO/001/2018 – የጨረታ ሰነዱ የሚከፈትበት እና የሚዘጋበት ቀን በ30/01/208 ዓ.ም በበ4፡15 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት በጽ/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል።
የግዥ መለያ ቁጥር PPPDSO/002/2018 – የጨረታ ሰነዱ የሚከፈትበት እና የሚዘጋበት ቀን በ03/02/2018 ዓ.ም በ4:15 ሰዓት ተዘግቶ፤ በ4:30 ሰዓት በጽ/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል። የተጠቀሱት ቀናት በዓላት ወይምዝግ ከሆኑ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጨረታው የሚከፈት ይሆናል።
7. የመሰረዝ መብት፦ መ/ቤቱ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ፡– የሀረሪ ህዝብ ከልል የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጽ/ቤት ሐረር አራተኛ አደባባይ 100 ሜትር ወረድ ብሎ በሚገኘው ዘቢዳ ሕንፃ አራተኛ ወለል።
ለበለጠ መረጃ የመ/ቤቱ አድራሻ፡– 09-15-09-98 03 ይደውሉ ወይም በ https://WWW.facebook.com/hppdso
website:- https://hppdso.gov.et Telegram:- https://t.me/hppds2
በሐረሪ ህዝብ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ሰጪ ጽ/ቤት