Your cart is currently empty!
የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ስራና ክህሎት ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ፈርኒቸር፣ ኤሌክትሮኒክስ፤ ሞተርሳይክል፤ የጽሕፈት መሣሪያዎች እና የጽዳት ዕቃዎች፣ የሞያ ደህንነትና ጤንነት የቁጥጥር መሳሪያዎችን (OSH) እና መጋረጃ እና ምንጣፍ ግዥ መፈጸም ስለሚፈልግ በዘርፉ ፍቃድ ያላቸውን ድርጅቶች አወዳድሮ ውል በማስገባት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 24, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/18
የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ስራና ክህሎት ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ሎቶችን ፈርኒቸር፣ ኤሌክትሮኒክስ፤ሞተርሳይክል ፤የጽሕፈት መሣሪያዎች እና የጽዳት ዕቃዎች፣ የሞያ ደህንነትና ጤንነት የቁጥጥር መሳሪያዎችን (OSH) እና መጋረጃ እና ምንጣፍ ግዥ መፈጸም ስለሚፈልግ በዘርፉ ፍቃድ ያላቸውን ድርጅቶች አወዳድሮ ውል በማስገባት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች:-
1. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
2. የዘመኑን ግብር የከፈለና አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው።
3. በፋይናንስ መስሪያ ቤቶች ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ ማንኛውም ተጫራች መሳተፍ ይችላል።
4. የተዘጋጀ ጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከመ/ቤቱ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) ብር ለእያንዳንዱ ሎት በመከፊል መግዛት ይችላል።
5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የቴክኒካል የጨረታ ሰነድና የፋይናንሺያል የጨረታ ሰነድን ለብቻ በተለያ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለእያንዳንዱ ተመሳሳይ አንድ አንድ ኮፒዎች አዘጋጅተው በየኤንቨሎፕ የውጭ ገጽ ዋና ኦርጂናል/ወይም/ ኮፒ ብሎ በመፃፍና አሽገው ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የመጨረቻ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት በፊት ብቻ ይሆናል። ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ በግልጽ ይከፈታል። ሆኖም 16ኛ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይሆናል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለስቴሽነሪ እና የጽዳት ዕቃዎች 10,000 (አስር ሺህ) ብር በባንክ በተረጋገጠ CPO፣ የባንክ ጋራንቲ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለኤሌክትሮኒክስ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) ብር በባንክ በተረጋገጠ CPO፣የባንክ ጋራንቲ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
9.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለፈርኒቸር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር በባንክ በተረጋገጠ CPO፣የባንከ ጋራንቲ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሞተርሳይክል 70,000 (ሰባ ሺህ) ብር በባንክ በተረጋገጠ CPO፣ የባንከ ጋራንቲ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሞያ ደህንነትና ጤንነት የቁጥጥር መሳሪያዎችን (OSH) 150,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ) ብር በባንክ በተረጋገጠ CPO፣ የባንክ ጋራንቲ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
12. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለመጋረጃ እና ምንጣፍ 120,000 (አንድ መቶ ሃያ ሺህ) ብር በባንክ በተረጋገጠ CPO፣የባንከ ጋራንቲ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
13. ጨረታውን በከፊል መጫረት የሚፈልግ ተጫራች ከተዘረዘሩት የዕቃ አይነቶች አንድ ወይም ከአንድ በላይ መርጦ መጫረት ይቻላል ።
14. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ/ጉ/አቅራቢ/ዎች/ተጨማሪ መረጃ የሚፈልጉ ከሆነ በስልክ ቁጥር 046 212 2174 ዘወትር በስራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ፡፡
15. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የመ/ቤቱ አድራሻ፦
ሀዋሳ መስቀል አደባባይ ከፍ ብሎ መናኃሪያ ሌዊ ሆቴል ፊት ለፊት ሲዳማ ቡና ህንጻ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 804
የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስራና ክህሎት ቢሮ