Your cart is currently empty!
የድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ተሽከርካሪ መኪና እና ሞተር ሳይክል ጥገና እና እድሳት አገልግሎት ስራዎች የሚያከናውኑ ባለጋራዦች ለአንድ አመት የሚቆይ ውል በአካባቢያዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል
Melekite Dire(Sep 24, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የተሽከርካሪ መኪና እና ሞተር ሣይክል ጥገና እና እድሳት ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ የጨ/መ/ቁ/መ/ል/ማ/ቢሮ 002/2018
የድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለ2018 በጀት ዓመት ከመንግስት በተመደበለት በጀት የተቋሙ
- ተሽከርካሪ መኪና እና
- ሞተር ሳይክል ጥገና እና
- እድሳት አገልግሎት ስራዎች የሚያከናውኑ ባለጋራዦች ለአንድ አመት የሚቆይ ውል በአካባቢያዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ስራ የተሠማሩና ሕጋዊ የንግድ ፍቃድና በመንግስት የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝግበው የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያቁጥርያላቸው
- ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ጨረታ አግባብነት ያለው የተሟላ ማስረጃና ሠነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ የጨረታ ሠነዱን ከፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 304 ቀርበው የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ/ በመክፈል መግዛትይችላሉ ፤ አስፈላጊውን ዋጋ በግልጽ ቫትን ያካተተ መሆን አለመሆኑን በመግለጽ ሞልተው ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዋናውና ኮፒውን በአግባቡ አሽገው ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛ ቀን ጠዋት ልክ 3፡00 ሠዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ ዕለት ልክ 3፡30 ላይተጫራቶችወይምሕጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት በሥራ ሂደቱ ቢሮ በግልጽ ይከፈታል
- ተጫራቾች ለተሽከርካሪ መኪና ብር ብር 20.000 /ሃያ ሺ/ እንዲሁም የሞተር ሣይክል ብር 10.0000/ አሥር ሺ/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም በባንክ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሊተር ኦፍ ክሬዲት እንዲሁም ከዳራጁት የመንግስት ተቋም በደብዳቤ በሚሰጥ ዋስትና ከነዚህ አማራጮች በአንዱ በመጠቀም ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያቤቱየተሻለመንገድካገኘጨረታውንበሙሉምሆነበከፊልየመሠረዝመብቱየተጠበቀነው፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያና መረጃ
የድሬዳዋ የመሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮ
የፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
ሞባይል፡- 0920423392/0910258250