Your cart is currently empty!
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢንጂነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ ፋይናንስ እና ግዥ መምሪያ የተሽከርካሪ ወንበር ልብስ ጨርቅ እና መረጋገጫ ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 26, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEP/EC/FP/NCB/05/2018
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢንጂነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ ፋይናንስ እና ግዥ መምሪያ ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን የተሽከርካሪ ወንበር ልብስ ጨርቅ እና መረጋገጫ ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ–ገጽ ላይ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት የካ ክ/ከ ወረዳ 9 ኮተቤ ብረታ ብረት ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና መ/ቤት፣ የኢንጂነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ ፋይናንስ እና ግዥ ቢሮ የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጹትን ዕቃዎች በሚመለከት የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/EC/FP/NCB/05/2018 የሚል ምልክት በማድረግ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
|
የአቅርቦት ግዥ ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
የተሽከርካሪ ወንበር ልብስ ጨርቅ እና መረጋገጫ ግዥ |
ብር 25,000.00 |
መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት |
መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡15 ሰዓት |
- ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር +251 116 73 21 98 መደወል ይችላሉ።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢንጂነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ ፋይናንስ እና ግዥ መምሪያ