Your cart is currently empty!
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የመኪና መለዋወጫ፣ የተለያየ ሳይዝ ያላቸው የመኪና ጎማና ባትሪ እና አመታዊ የመኪና ኢንሹራንስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አመታዊ ውል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 27, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በ2018 የበጀት አመት ለጎንደር ከተማ አስተዳደር አገልግሎት ለምንሰጣቸው ሴ/መሰሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል
- በሎት 1 የመኪና መለዋወጫ
- በሎት 2 የተለያየ ሳይዝ ያላቸው የመኪና ጎማና ባትሪ
- በሎት 3 አመታዊ የመኪና ኢንሹራንስ
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አመታዊ ውል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን፡-
ማቅረብ የምትችሉት መረጃ፦
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው
- የሚገዛው የመኪና መለዋወጫ ጎማ ባትሪና የኢንሹራንስ አገልግሎት የገንዘብ መጠን ከ200,000/ሁለትመቶ ሽህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የሚገዛውን የመኪና መለዋወጫ ጎማና ባትሪ እንደዲሁም የኢንሹራንስ አገልግሎት ዝርዝር መግለላጫ /ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ/ ቢድ ቦንድ/ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 1% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100/መቶ ብር/ በመክፈል ጎን/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 7 መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሃሳባቸውን አንድ ወጥ በሆኑ ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በመሙላት በታሽገ ፖስታ ጎን/ከ/አስ/ግዥና ንብ አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ዋጋውን በሚሞሉበት ወቅት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ሙሉ ስምና ፊርማቸውን የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በጎንደር ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 11 በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ። ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት ይከፈታል። የጨረታው መክፈቻ ቀን ህዝባዊ በዓልሳምታዊ የረፍት ቀናት ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት በተጠቀሰው ሰዓት የሚዘጋና የሚከፈት ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች የሚቀርብ ቅሬታ ካለ ጨረታው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 የስራ ቀን ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ከ5 የስራ ቀናት በኋላ የሚቀርብ ቅሬታ የማንቀበል መሆኑን እንገልጻለን።
- ለተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ ጎን/ከተ/አስ/ ግንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 126 03 06 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
- የመኪና መለዋወጫው ጎማና ባትሪ እንዲሁም የኢንሹራንስ አገልግሎቱ በሚፈለግበት ወቅት ጎን/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች መጫረት መወዳደር የሚችሉት የንግድ ዘርፍ በሚመለከታቸው ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
ማሳሰቢያ፡-አሸናፈው ተጫራች የሚያቀርበው እቃ ኦርጅናልና በወጣው አስፔስፊኬሽን መሰረት ይሆናል ።
አሸናፊ የሚለየው በሎት ጠቅላላ ዋጋ ነው።
ከተዘረዘሩት ውስጥ አንዱን ያልሞላ ከውድድር ውጪ ይሆናል።
P.O. box: 192 Tele-0581-26-03-06
Fax:0581-11-75-63
email:- gontipco@ethionet.et
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ