Your cart is currently empty!
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት ቋሚ ዕቃ እና የሠራተኞች ካፌ አገልግሎት በ2018 በጀት አመት ለወረዳው ጽ/ቤቶች አገልግሎት መስፈርቱን የሚያሟሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 29, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 002/ 639/2017
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ቋሚና የሠራተኞች ካፌ አገልግሎት በ2018 በጀት አመት ለወረዳው ጽ/ቤቶች አገልግሎት መስፈርቱን የሚያሟሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል።
- ሎት 1. የሠራተኞች ካፌ አገልግሎት
- ሎት-2. ቋሚ ዕቃ
በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱት መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ጨረታው ላይ እንዲሳተፉ ይፈልጋል።
1. ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-2 ለተጠቀሱት እቃዎች እና አገልግሎቶች አግባብነት ያለው ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑ ግብር የከፈሉ እንዲሁም የታደሰ የዘመኑ ንግድ ፈቃድ እና የምዝገባ ወረቀት ኮፒ በገቢዎች የጨረታ መሳተፊያ ጊዜን የሚገልጽ ደብዳቤ ያለው በአቅራቢነት የተመዘገቡ እንዲሁም 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በላይ ዕቃ /አገልግሎት/ የሚያቀርቡ ድርጅቶች የቫት /VAT ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
2. ተጫራቾች ይህን ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት አስኮ ኖክ ማደያ አለፍ ብሎ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ ፋይናንስ በመገኘት ለእያንዳንዱ ሰነድ 200 ብር ( ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ትችላላችሁ።
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (1%)ቱን ያለውን የእቃውን ዋጋ ወደ ብር ተቀይሮ እያንዳንዱ በሎት1 1% 5000 ለሎ2 1% 5000 በባንክ በተረጋገጠ (Cpo) ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በፖስታ በማድረግ ጨረታው በአየር ላይ እስከ ዋለበት የመጨረሻ ቀንድረስ እስከከቀኑ 11፡30 ሰዓት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
4. ተጫራቾች የእያንዳንዱ እቃ የሚሸጡበት ዋጋ በመግለፅ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ሙሉ አድራሻውን ስማቸውንና የጨረታ አይነት በመጥቀስ የድርጅቱን ማህተም በመሳረፍ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች የተጠቀሱት እቃዎች ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል መጫረት ይችላሉ።
6. የጨረታው ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ቀን ጨረታው በጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ይሆናል።
7. ጨረታው በ11ኛው ቀን ማለትም ቅዳሜ፣ እሁድ እና በዓላት ቀናት ላይ ከዋለ በቀጣይ የስራ ቀናት ላይ ከጠዋት 2፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው ፋይናንስ 1ኛ ፎቅ የሚከፈት ይሆናል።
8. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫት ያካተተ መሆን አለበት።
9. ወረዳው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. ተጫራቾች ለክፍያ ስትመጡት ደረሰኛችሁ ብርሃንና ሰላም የታተመ መሆን እንዳለበት አውቃችሁ ከወዲሁ ዝግጅት እንድታደርጉ
11. ተጫራቾች የገዙት የድርጅቱ ሙሉ ሰነድ ሁሉም ገጽ ላይ የተቋሙን ማህተም በማድረግ ጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸው።
አድራሻ ፡– አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት አስኮ ኖክ ማድያ አለፍ ብሎ
ስልክ ቁጥር 09-84-659-144
ማሳሰቢያ፡– እያንዳንዱ ሰነድ በየሎቱ በተለያዩ ፖስታ ተሞልቶ ማቅረብ አለበት፡፡ እንዲሁም ጨረታው ከመታሸጉ በፊት የጨረታ ሰነዱንና ሳንፕሎችን መቅረብ አለባቸው፡፡ ከጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ በሚያመርቱት ምርት እና ካደራጃቸው አካል በሚቀርበው ሕጋዊ ድጋፍ በንግድ ዘርፉ በተሰማሩበት (በሚቀርበው ድጋፍ ደብዳቤ መሠረት) ይስተናገዳሉ።
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት