Your cart is currently empty!
ናሽናል ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበር የጉምሩክ አስተላላፊዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል
Reporter(Oct 12, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የጨረታ ማስታወቂያ
ናሽናል ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበር የጉምሩክ አስተላላፊዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች:-
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው ፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ቢያንስ ከ4 ድርጅቶች ጋር በመሰል ዘርፍ እየሰራ ያለና የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ፣ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ያለውና ለመሆናቸው ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ።
2, ከታች በቁጥር 2.1 እና 2.2 የተዘረዘሩትን የጅቡቲ ወደብና የጉምሩክ ማስተላለፍ ለተገለጹ ስራዎች በታሸገ ፖስታ የእያንዳንዱ ዋጋ በግልጽ በማስቀመጥ ሳር ቤት ግደይ ገ/ህይወት ህንጻ 3ኛ ፎቅ አ.አ. ስልክ፡ 251 11 442-1928/ 09 30-30-41-10 ግዢ ክፍል እና ድሬዳዋ ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ስልክ ቁጥር 09 35-98-50-83/ 09 30-28-34-90 ግዢ ክፍል በታሸገ ፖስታ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
2.1. የጅቡቲ ወደብና የማስተላለፍ አገልግሎት ክፍያ(Djibouti port fee & Clearance fee)
የጅቡቲ ወደብ ወጪ ያለምንም ዲመሬጅና የወደብ መጋዘን ክፍያ
- ለ 40 ፊት ኮንቴነር
- ለ 20 ፊት ኮንቴነር
- ለ 40 ፊት ኮንቴነር (ፈንጂዎች፣ ተቀጽላዎች እና ተቀጣጣይ የመሳሰሉትን የጫነ
- ለ 20 ፊት ኮንቴነር (ፈንጂዎች፣ ተቀጽላዎች እና ተቀጣጣይ የመሳሰሉትን የጫነ
- መጠናቸው ትላልቅ ለሆኑ እቃዎች (Break bulk cargo (including machineries)
- በልዩ ሁኔታ ለሚጫኑ እቃዎች (Special cargos which need direct delivery (heavy items)
- Import raw materials including coal (per ton)
2.1. 2.2 የጉምሩክ ማስተላለፍ አገልግሎት ክፍያ/Customs clearing service /ለሀገር ውስጥ)
- ለ 40 ፊት ኮንቴነር
- ለ 20 ፊት ኮንቴነር
- መጠናቸው ትላልቅ ለሆኑ እቃዎች
- ኤክስፖርት በቶን ወይም በቮልዩም
- በበልክ ለሚጫኑ እቃዎች እና
- በአዲስ አበባ ኤርፖርት በኩል ለሚገቡ እቃዎች
3. ተጫራቾች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 3 ተከታታይ ወራት ህጋዊ ሆኖ የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. 50,000.00 /ሀምሳ ሺህ ብር/ ወይም የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
4. የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ባሉት 20 የስራ ቀናት የሚቆይ ሆኖ ማለትም ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ጨረታው ተዘግቶ ጥቅምት 21/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ በሚገኘው ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
5. ጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
6. ተጫራቾች ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 251 11 442-1928/ 09 30-30- 41-10 / 09 35-98-50-83/ 09 30-28-34-90 እንዲሁም በግዢ አቅርቦትና ንብረት አስተዳደር ክፍል በስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 -6፡00 እና ከሰዓት 8፡00–11፡30 ማግኘት ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡-
- አሸናፊ ተጫራች አገልግሎቱን ለመስጠት የሚጠቀምበት ቢሮ ፋብሪካው በሚገኝበት ድሬዳዋ እና የተሟላ ብቁ የሰው ሀይል እንዳለው ወይም
እንደሚያሟላ ማረጋገጥ ይጠበቅበታል፡፡ - ተጨራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ተከፍቶ ውሳኔ ይሰጥበታል፡፡ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመስረዝ መብት አለው፡፡
ድርጅቱ