Your cart is currently empty!
አዋሽ ወይን አ.ማ. ከ 16,000 ሊትር በላይ ፍሳሽ የሚያመላልስ መኪና አገልግሎት ይፈልጋል
Reporter(Oct 12, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የአዋሽ ወይን አ.ማ. የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ
አዋሽ ወይን አማ. በ1936 ዓ.ም. የተመሰረተ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የወይን ፋብሪካ ሲሆን አዋሽ፤ ጉደር፤ አክሱሚት፤ ከሚላና ገበታ የተባሉ የወይን ምርቶችንና ዳንኪራ የወይን ኮክቴልን በማምረት ለህብረተሰቡ በማቅረብ ይታወቃል።
አዋሽ ወይን አማ. በድርጅቱ ግቢ ማለትም ከመካኒሳ አዋሽ ወይን ጠጅ ፍብሪካ በማምረት ሂደት ዉስጥ የሚመረተውን የፍሳሽ ቆሻሻ ከማጠራቀሚያው ጉድጓድ (septic tank) በማንሳት ልደታ በሚገኘው የወይን ጠጅ ፋበሪካችን ዉስጥ የፍሳሽ ዉሃ ማከሚያ ፕላንት በመገልበጥ ይሆናል :: እንዲሁም ከልደታ ቅርንጫፍ ወደ ታወቀ የስላጅ መድፊያ ቦታ ጭቃውን ፓምፕ በማድረግ መውሰድ ይሆናል:: በመሆኑም ይህን ፍላጎቱን ለማሳካት ከ 16,000 ሊትር በላይ ፍሳሽ የሚያመላልስ መኪና፤ ብቁና ተገቢው የስራ ልምድ ያለውና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎች የሚያሟላ ማንኛውንም ተጫራች አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
መስፈርቶች
- የታደስ ንግድ ፈቃድ፤ የግብር መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት፤ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ህጋዊ ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚችል
- የሚያቀርበው የፍላሽ መኪና ለስራው ብቁ መሆን ይጠበቅበታል(designed for liquid waste transport)
- ተወዳዳሪው በስራዉ ላይ በቂ ልምድና ችሎታ ያለው መሆን ይጠበቅበታል
- በቀን ዉስጥ የሚያመርተውን የፍሳሽ ቆሻሻ ሙሉ በሙሉ ማንሳት።
- ደህና ይዞታ ላይ ያለ የፍሳሽ ማንሻ መኪና ማቅረብ የሚችል።
- በሚጭንበት፡ በሚያራግፍበትና በሚንቀሳቀስበት ቦታ ፍሳሽ ማንጠባጠብ የለበትም።
- ለስራው በቂ የሰው ሃይል መመደብ የሚችል
- ከፍሳሽ አወጋገድ ጋር ያለውን ሃገራዊ ህጎች የተገነዘበ መሆን ይኖርበታል
- የተሰጠውን ስራ በሃላፊነት የሚስራ፡ እና ድርጅቱን ከአሉታዊ ተፅዕኖ የሚጠብቅ (ከተፈቀደ ማራገፊያ ዉጭ አለመጠቀም፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ፈቃድ መጠየቅ)
- የድርጅቱን የስራ ላይ ደህንነት እና የአካባቢ አያያዝ ህጎችን የሚከብርና የሚጠብቅ
- ለሚያሰራቸው ሰራተኞቹ በቂ የስራ ላይ ደህንነት ቁሳቁሶችን ማቀረብ የሚችል (ጫማ፣ አንፀባራቂ፣ ግላብ፣ የስራ መነፀር)
ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉና ፍላጎቱ ያላችሁ ተጫራቾች የተዘረዘሩትን ሰነዶች ወይም ማስረጃዎች እና የዋጋ ዝርዝር መስጫ በአንድ ጉዞ በመያዝ መካኒሳ በሚገኘው አዋሽ ወይን ጠጅ አ.ማ. ዋና መስሪያ ቤት ግዢ ክፍል በአካል በመምጣት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እንድታስገቡ እንጠይቃለን:: ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0918913895 ወይም 0966334557 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡-
- አዋሽ ወይን አማ. ይሄን ማስታወቂያ በሙሉም ሆነ በከፊል የመቀየር ወይም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አዋሽ ወይን አ.ማ. የተሻለ መንገድ ካገኘ የንግድ ማንኛውንም አመልካች መስፈርቶቹን የሚያሟላ የመምረጥ መብቱ የተጠበቀ ነው።