የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በየካ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በኮልፌ ቀራንዮ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በአዲስ ከተማ፣ ለሚ ኩራ፣ በጉለሌ እና ቦሌ ክ/ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ይፈልጋል


Addis Lessan(Oct 11, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

የ7ኛ ዙር መሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በየካ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በኮልፌ ቀራንዮ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በአዲስ ከተማ፣ ለሚ ኩራ፣ በጉለሌ እና ቦሌ ክ/ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች

1. ለአንድ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 2300.00 (ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ብር)landleasedocument.aalb.gov.et  በመባት በኦን ላይን በቴሌ ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከ ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ።

2. ማንኛውም በዚህ የመሬት ሊዝ ጨረታ ለመሳተፍ የፈለገ ተጫራች በተራ ቁጥር 1 ላይ በተገለጸው ዌብ ሳይት በመግባት የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በመጀመሪያ በስሙ የቴሌ ብር አካዉንት በመከፈት ከአካዉንቱ ተቀናሽ በማድረግ ሰነዱን መግዛት ይጠበቅበታል።

3. ተጫራቾች ቦታዎቹ የሚገኙበት ቦታ በመሄድ አጠቃላይ የቦታዎችን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ አለባቸዉ።

4. አንድ ተጫራች በአንድ የጨረታ ዘር ከአንድ ቦታ በላይ መጫረት አይችልም። በመሆኑም ከአንድ በላይ ቦታ ተፈርቶ ከተገኘ ተጫራቹ ከጨረታ ውጪ ይሆናል።

5. ተጫራቾች ሞልተዉ የሚያቀርቡት የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ላይ በቀረበው መስፈርት መሠረት መሆን ይኖርበታል።

6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ቦታ ስፋት በመነሻ ዋጋ ተሳስቶ ከሚገኘው ጠቅላላ ዋጋ 50% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ለየቦታ ኮዱ በጋዜጣው ላይ የተቀመጠውን መጠን ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም ከ50 ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል። እንዲሁም አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም። ከአዲስ አበባ ውጪ ከሚገኙ ባንኮች ሲርአ ስታሰሩ አዲስ አበባ ከሚገኙ ባንኮች በኔትዎርክ የተያያዘ መሆን አለበት ይህ ሳይሆን ቀርቶ ችግር ቢፈጠር መ/ቤቱ አይጠየቅም።

7. ተጫራቾች የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ ስትመለሱ

7.1 ኦርጅናል ሲፒኦ (cpo)

7.2 የመስሪያ ቤቱ ማህተም ያረፈበት የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ

7.3 የተጫራቹ መታወቂያ ኮፒ

7.4 ሰነድ ለመግዛት በቴሌ ብር የተከፈለበት ስሊፕ (ደረሰኝ)

7.5 ኦርጅናል የአቅም ማሳያ ማስረጃ

7.6 ተጫራቹ የሚመረተው በተወካይ ከሆነ የተወካይ መታወቂያ እና የውክልና ማስረጃ ኮፒ

7.7 የውጭ ሀገር ዜግነት ያለው በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነ ማንኛውም ተጫራች ከሚኖርበት ሀገር በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቆንስላ ጽ ቤት የተሰጠውንና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ የፀደቀ መታወቂያ (Yellow Card) የዋናውን ኮፒ ከመልስ ማቅረቢያው ጋር ማያያዝ አለበት።

7.8 የንግድ ማህበራት ለሆኑት በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ፅ/ቤት የፀደቀ የማህበሩን መመስረቻ ጽሑፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ፎቶ ኮፒ ሌሎች ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶች ከሆኑ ህጋዊነታቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ እና የታደሰ ምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ

7.9 ጨረታውን የሚሳተፉት ባልና ሚስት በአንድ ሰነድ ከሆነ ህጋዊ የጋብቻ ማስረጃ ኮፒ እና በአንድ ወገን ስም የተሰራ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒአ ማቅረብ አለባቸዉ።

7.10 በአንድ የጨረታ ሰነድ ከአንድ ሰው በላይ ሆነው ለመወዳደር ከፈለጉ ከሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ዕ ቤት የተረጋገጠ የተደራጁበትን ህጋዊ ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

7.11 በአጠቃላይ ከላይ ከተራ ቁጥር 6.1 እስከ ተራ ቁጥር 6.10 የተገለጹትን ማስረጃዎች ዋና ኦርጅናል) እና ኮፒ እያንዳንዳቸውን ለየብቻ በማሸግ እና በፖስታዎቹ ላይ የተጫራች ስም፣ የጨረታ ቁጥር እና የቦታ መለያ ኮድ በመፃፍ ሁለቱን ፖስታዎች በአንድ ፖስታ በማሸግ – ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለም ሆቴል አከባቢ ኤም ኤ (MA) ህንፃ ላይ በሚገኘው በከተማው መረት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ተጫራቾች ሞልተው የሚያቀርቡት የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የተሞላው ዋናው ኦርጅናል) እና ኮፒ መካከል የጽሑፍ ልዩነት ቢፈጠር ዋና ኦርጅናል) ሰነዱ ገዥ ይሆናል።

8. ጨረታውን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በ5 ተከታታይ ቀናት በቦሌ ክ/ከተማ አስተደዳር አዳራሽ የሚከፈት ሆኖ ዝርዝሩ በውስጥ ማስታወቂያ ይገለፃል። ተጫራቾች ቦታውን በአካል ለመመልከት ከፈለጉ በ04/02/18 ዓ.ም ፣ በ6/02/18 ዓ.ም እና በ10/02/18 ዓ.ም ጠዋት ከ3፡00 ሰዓት – 6፡30 ሰዓት እና ከሰዓት 8፡00 ሰዓት – 11፡30 ሰዓት ለጨረታ የተዘጋጁ ቦታዎች በሚገኙበት ከ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ ለዚህ ስራ በሚመደቡ አስጎብኝዎች አማካኝነት ቦታዎቹን መመልከት ይቻላል።

9. ጨረታውን ያላሸነፉ (ተሸናፊ) ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ሲፒኦ የጨረታው አሸናፊዎች በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ከተገለፀበት ከ15 የስራ ቀናት በኃላ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ መ/ቤቱ (ቢሮው) ለባንክ በመላክ ወዳሰሩበት የባንክ ሂሳብ ተመላሽ ይደረጋል። በካሽ ያሰሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናውን ለመረከብ በቅድሚያ የሲፒኦውን ጉርድ ኮፒ ማቅረብና ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቀርበው መውሰድ አለባቸው። ከላይ በተገለጸዉ የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርበው ካልወሰዱ ለሚፈጠረው ችግር አጫራቹ መ/ቤት ተጠያቂ አይሆንም።

11 መስሪያ ቤቱ (ቢሮው) የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ፡

በስልክ ቁጥር +251111570595 Website: https://www.aalb.pov.et/   

Telegrm:- t.me/addisland

Facebook:- Addis Ababa City Land Development Administration and Bureau

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *