Your cart is currently empty!
የደብረ ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተቆረጠ ግንድ የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖችን በዘርፉ የተሰማሩ ባለንብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ባለንብረት ጋር የኮንትራት ውል በመግባት ግንዱ ተጭኖ እስከሚያልቅ ድረስ ለመከራየት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 12, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ለሚያመርተው ቬኒር እና ፕላይ ውድ ጣውላ ግብዓት የሚሆን የባሕርዛፍ ግንድ ጫካው ከሚገኝበት ከደ/ብርሃን ወደ ደሴ በሚወስደው መንገድ ከሚገኘው ቀይት ቀበሌ ልዩ ስሙ አመር አገር አካባቢ እና ቀይት ቀበሌ ልዩ ስሙ አይሶፌ መድኃኒዓለም አካባቢ ደን ሳይት የተቆረጠ ግንድ የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖችን በዘርፉ የተሰማሩ ባለንብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ባለንብረት ጋር የኮንትራት ውል በመግባት ግንዱ ተጭኖ እስከሚያልቅ ድረስ ለመከራየት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት፡-
1. በዘርፉ የተሰማራና የንግድ ሥራ ፈቃዱን ያሳደሰ እና ስድስት ወር ያላለፈው ጨረታ ለመሣተፍ የሚያበቃ የገቢዎች የጨረታ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው
- የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለሁለቱም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 60,000.00 /ስልሣ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
- በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ምንም ዓይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለም አንድ ሰረዝ በማድረግ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
- ድርጅቱ ክፍያ የሚፈፅመው በቢያጆ ስለሆነ ለመኪናው የሚያስፈልገውን ወጭ የነዳጅ እና ሌሎች ሁሉንም ወጭዎች የሚሸፍነው ባለመኪናው ይሆናል፣
- ተጫራቾች ኦሪጅናል የጨረታ ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ውስን ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት የሚቆይ ስለሆነ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ገቢ ማድረግ ይችላሉ።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ ውስጥ በይፋ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ከመከፈት አይታገድም።
- የመክፈቻ ቀኑ የሕዝብ በዓል ወይም እሁድ ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ማስያዝ አለበት።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁፕር 0910368437 ደውለው ይጠይቁ
የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር
ደብረ ብርሃን