Your cart is currently empty!
በአብክመ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የሀርቡ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ስቴሽነሪ፣ የፅዳት እቃ፣ ልዩ ልዩ የእጅ መገልገያ መሳሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 14, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የሀርቡ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ ቤት ለሀርቡ ከተማ የ2018 በጀት አመት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ሎቶች መሰረት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1. ስቴሽነሪ፣
- ሎት 2 የፅዳት እቃ፣
- ሎት 3 ልዩ ልዩ የእጅ መገልገያ መሳሪያ፣
- ሎት 4 ኤሌክትሮኒክስ፣
- ሎት 5 ፈርኒቸር
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
1. በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው
2. የግዥ መጠኑ 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ /ብር በላይ የቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
3. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪል ከተራ ቁጥር 1-2 ላይ የተጠቀሱትን ኦርጅናል ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 4/02/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 18/02/2018 ዓ.ም 11፡30 ድረስ ሀ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት አባይ ባንክ አንደኛ ፎቅ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 ብር በጥሬ ገንዘብ በመክፈል የሚፈለገውን የእቃ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (እስፔስፊኬሽን) የያዘ የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚችሉ ሲሆን ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የሚያቀርቡት ዋጋ ከነቫቱ ነው፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በየሎቶቹ ለየብቻ በመለየት የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2 % ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው የሚያስዙት የጨረታ ማስከበሪያ በቢድቦድ ከሆነ ከ60 ቀን ያነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድቦንድ ተቀባይነት የለውም፡፡
6. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን እቃዎች አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀናት ጀምሮ ካሉት 5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የዋጋውን የውል ማስከበሪያ በየሎቱ 10% በማስያዝ ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
7. የጨረታ ውድድር የሚያካሄደው በሎት ወይም በጥቅል ድምር ውጤት ስለሆነ የማይሞላ አይተም (እቃ) መኖር የለበትም፡፡
8. ተጫራቾች በየሎቱ በተለያየ ፖስታ በማሸግ የጨረታ ሰነድን ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ የሀርቡ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት አባይ ባንክ 1ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ በማስገባት ሳጥኑ የሚታሸግ ሲሆን በ19/02/2018 ዓ.ም 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልጽ ይከፈታል፤ ከተጠቀሰው ቀንና ሰአት ዘግይቶ የሚመጣ ተጫራች የጨረታ ሰነዱ ተቀባይነት የሌለው ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በመከፈቻው ዕለት የማይገኙ ከሆነ በሌሉበት ይከፈታል የጨረታ መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን እና ሰአት የሚከፈት ይሆናል፡፡
9. ሁሉም የጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማ መኖር የሚገባው ሲሆን ስርዝ ድልዝ ሲያጋጥም በፊርማ ማረጋገጥ ይጠበቅባችኋል፡፡
10. መ/ቤቱ ካሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ካሸነፈው እቃ ወይም ገንዘብ መጠን ላይ 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
11. ተጫራቾች ክልሉ ላወጣቸው የግዥ አፈጻጸም መመሪያዎች ተገዥ መሆን ሲኖርባቸው ማሸነፉ ከተነገረ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራስን ማግለል አይቻልም፡፡
12. አሸናፊ ድርጅት ንብረቱን በሀርቡ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ግዴታ ይሆናል።
13. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡
14. አሸናፊው ተጫራች ኦርጅናል እቃዎችን የማቅረብ ግዴታ ያለበት ሲሆን እቃዎቹን የምንቀበለው በሚመለከተው ባለሙያ ሲረጋገጥ ነው።
15. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር ማስረጃ ከፈለጉ ሀርቡ ከተማ አስተዳደር ግ/ፋ/ን/አስ/ አባይ ባንክ አንደኛ ፎቅ ላይ በአካል በመገኘት ወይንም በስልክ ቁጥር 033 552 0883 / 09 21 03 12 72 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡- በማንኛውም ሁኔታ የተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ በሚከፈትበት ሰዓት የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡
በደቡብ ወሎ ዞን የሀርቡ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ ቤት