Your cart is currently empty!
የአመድጉያ የበግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን መሪ የበጎች የተመጣጠነ መኖ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 14, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የአመድጉያ የበግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን መሪ የበጎች የተመጣጠነ መኖ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
እነዚህን ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ የንግድ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን መ/ቤቱ ይጋበዛል፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN Number/ተመዝጋቢና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. ጠቅላላ ግዥው ወይም ዋጋው ከ200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT)ተመዝጋቢና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. ተጫራቾች በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት መድሃኒትና መኖ አስተዳደር ቁጥጥር ባለስልጣን የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ የመወዳደሪያ ዋጋቸውን በመሞላትና በማሸግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት አዲስ አበባ ግብርና ሚኒስቴር ድረስ በመምጣት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
7. የሚገዙ ዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር ስፔስፊኬሽን መ/ቤታችን በአማርኛ ቋንቋ ያዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 50 (ሃምሳ)ብር በመክፈል መግዘት ይቻላሉ፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድ ቦድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንከ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ/ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችል እና በጨረታው ላይ ችግር ቢከሰትና ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ በራሱ ምክንያት ውል ባይፈፅም ያስያዘውን የጨረታ ማስከበሪያ የሚወረስ መሆኑንና አቅርቦቱን ካሸነፈ ለውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ የሚችል፡፡
9. ተጫራቾች የተመጣጠነ የበጎች የመኖ ዋጋ ሲሞሉ መ/ቤቱ ድረስ የማጓጓዣ፣ የማስጫኛና የማውረጃ አብሮ መሞላት አለባቸው፡፡
10. ተጫራቾች የበጎች የተመጣጠነ ፉርሽካ( መኖ )የሚጓጓዘው ተወዳዳሪው ድርጅት ካሸነፈበት ቦታ እስከ አመድጉያ የበግ ብዜት ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል ድረስ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ፡፡
11. ተጫራቾች የሚመረተው ፉርሽካ(መኖ) በንጥረ ምግብ ይዘቱ መሰረት መሆኑንና በላብራቶሪ (ፓስተር) እንደሚታይ (እንደሚመረመር) ማወቅ አለባችሁ፡፡
12. ተጫራቾች የተመጣጠነ መኖውን ከጨረታ ሰነዱ ማየት ይችላሉ፡፡
13. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነት ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርቦ የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ/ሲፒኦ/ (በጥሬ ገንዘብ)ማስያዝና ውል መፈፀም አለበት፡፡
14. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሁለት ኮፒ የሚመለከታቸውን ሰነዶች በሙሉ በማድረግ ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
15. የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በአየር ላይ ቆይቶ የጨረታ ሳጥኑ በማግስቱ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ግብርና ሚኒስቴር ቢሮ ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ይታሸጋል፡፡ በዚሁ እለት 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
16. ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም ጽ/ቤቱ ጨረታውን የሚከፍት ይሆናል፡፡
17. መ/ቤታችን ከሚገዛው እቃ 20%/ሃያ ፐርሰት/መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
18. ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
19. ለተጨማሪ ማስረጃ በስልክ ቁጥር 0912 166 555 / 0923 469 731 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በሰሜን ሸዋ ዞን በመ/ጌ/ም/ወረዳ አመድ ጉያ በግ/ብ/ዝ/ማ/ማእከል