Your cart is currently empty!
የአምሀራ ሳይንት አጅባር የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል መድሀኒት እና የህክምና እቃዎች፣ የፅህፈት መሳሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የፅዳት እቃ፣ ህትመት፣ የመኪና እቃዎች፣ ደንብ ልብስ እና ቋሚ የቢሮ እቃዎች /ፈርኒቸር/ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 14, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ ደ/ወሎ ዞን የአምሀራ ሳይንት አጅባር የመ/ደ/ ሆስፒታል በሎት ከፋፍሎ ጨረታ በማውጣት ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል ስለዚህ
- ሎት1 መድሀኒት እና የህክምና እቃዎች
- ሎት 2 የፅህፈት መሳሪያ
- ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ
- ሎት 4 የፅዳት እቃ
- ሎት 5 ህትመት
- ሎት 6 የመኪና እቃ እቃዎች
- ሎት 7 ደንብ ልብስ
- ሎት 8 ቋሚ የቢሮ እቃዎች ፈርኒቸር/
ስለዚህ
1. በዘርፉ የታደሰ አግባብ ያለው የንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት
2. የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር ቲን ሰርተፊኬት ያለው/ያላት
3. የግዥ መጠኑ ወይም የአገልግሎት መጠኑ ብር 200.000 እና በላይ ከሆነ የቫት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ ክዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
4. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200(ሁለት መቶ ብር) ሣይንት አጅባር የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 95 በመምጣት የጨረታ ሰነድን መግዛት ይቻላል ሰነዱን ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላት ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት ጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት እቃ ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 1% በሲፒኦ ወይም በሳይንት አጅባር የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ደረሰኝ በመቁረጥ ደረሰኙን ኮፒ በማድረግ ከሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል።
6. ጨረታው የሚከፈተው ጊዜ የህዝብ በዓላት ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
7. ሎት 1. መድሀኒት እና የህክምና እቃዎች ጨረታው የሚዘጋው በ19/02/2018 ዓ/ም በ4፡00 ይዘጋል በ19/02/2018ዓ/ም 4፡30 ይከፈታል።
8. ሎት 2 የፅህፈት መሳሪያ ጨረታው የሚዘጋው በ20/02/2018 ዓ.ም በ4፡00 ይዘጋል፤ በ20/02/2018 4:30 ይከፈታል።
9. ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ ጨረታው በ21/02/2018 ዓ.ም በ4፡00 ይዘጋል በ21/02/2018 4:30 ይከፈታል።
10 ሎት 4 የጽዳት እቃ ጨረታው በ24/02/2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ይዘጋል በ24/02/2018 4:30 ይከፈታል።
11. ሎት 5 ህትመት ጨረታው በ25/02/2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ይዘጋል በ25/02/2018 4:30 ይከፈታል።
12. ሎት 6 የመኪና እቃ እቃዎች በ26/02/2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ይዘጋል በ26/02/2018 4:30 ይከፈታል።
13 ሎት 7 ደንብ ልብስ 27/02/2018 ዓ.ም በ4፡00 ይዘጋል በ27/02/2018 4:30 ይከፈታል
14. ሎት 8 /ፈርኒቸር/ ጨረታው በ28/02/2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ይዘጋል በ28/02/2018 በ4፡30 ይከፈታል።
15. ማንኛውም ተጫራች ግዥው/ አገልግሎቱ በጥቅል ሎት ስለሆነ በተዘጋጀው ዝርዝር እቃ ውስጥ ካልሞላ ከውድድር ውጭ ይደረጋል።
16. የንብረት ርክክብ የሚደረገው የሚፈፀመው በሳይንት አጅባር የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሲሆን የማጓጓዣና የመጫኛና የማውረጃ ወጭ አሸናፊ ድርጅት ይሸፍናል።
17. በጨረታው ቀን ተጫራቾች ወይም ወኪሉ ባይገኝም ጨረታው አያስተጓጉልም።
18. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገን ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
19. ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 033 447 0422/033 447 0421 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የአምሀራ ሳይንት አጅባር የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል