Your cart is currently empty!
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የምስራቅ ባሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ2018 የበጀት ዓመት የሚያስፈልገውን ቋሚና አላቂ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 14, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግልጽ ጨረታ መለያ ቁጥር 001/2018
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የምስራቅ ባሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ2018 የበጀት ዓመት የሚያስፈልገውን ቋሚና አላቂ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት1፡– የጽሕፈትና ህትመት መሳሪያዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የቢሮ ቋሚ አላቂ እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ፈርኒቸር እቃዎች፣ የመኪና ጎማ፣ ለቢሮ ጥገና የሚውሉ ዕቃዎች፣ የቢሮ ምንጣፎች፣ ወዘተ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በተሠማሩበት የሥራ መስክ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸውና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋገጥ የምዝገባ ሰርተፊኬት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የግብር ከፋያ መለያ ቁጥር (ረሓም) ያላቸውና ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ሪሀረ) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ወደ መ/ቤታችን ግቢ ማድረስ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገለግል የመጫረቻ ዋጋ 3% በድርጅቱ ስም ሲፒኦ (ህሠሞ) በማዘጋጀት ማረጋገጫውን ከመወዳደሪያ ሠነዶቻቸውጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በአንድ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በግልጽ የጨረታ ሰነድ ላይ በጥንቃቄ ሞልተው በመፈረምና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋና እና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልቶ እና የድርጅቱን ሕጋዊ ማህተም አድርጐ የማያቀርብ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም።
- የጨረታው አሸናፊ ማሸነፋቸውን በጽሁፍ የምንገልጽላቸው ሲሆን ለጨረታ አፈጻጸም ማስከብሪያ ላሸነፉበት እቃ 10% በማስያዝና ውል በመዋዋል የተመረጡትን እቃዎች ሙሉ በውሉ መሠረት ካላቀረቡ በግዥ ሕጉ መሠረት መ/ቤቱ ተጠያቂ ያደርጋል።
- በጨረታው ያላሸነፉ ድርጅቶች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች በቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል እንደማይችሉ ማወቅ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የያዘ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከመስሪያ ቤቱ ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታው ሣጥን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት በምስራቅ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክፍል ሶስት (3) ቢሮ በግልጽ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የካታሎግ ናሙና ማቅረብ አለባቸው ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ናሙና ማቅረብ አይቻልም፤ ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ከውድድር ውጪ ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው እቃዎች በሙሉ ኦሪጅናል ሆኖ ለዚህም ዋስትና መቅረብ አለባቸው።
- የማስጫኛ እና የማስወረጃ ወጪ በተጫራቹ ይሸፈናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ ማብራሪያ፡– አድራሻ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሶስት መቶ ሜትር ከፍ ብሎ
ስልክ ቁጥር 0913396236 /0906350331
በምስራቅ ባሌ ዞን ጊኒር ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አምሳ ሜትር ከፍ ብሎ
የምስራቅ ባሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
cttx Building and Finishing Materials cttx, cttx Carpets and Curtains cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Construction and Water Works cttx, cttx Construction Machinery and Equipment cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx House Furniture cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Office Furniture cttx, cttx Office Machines and Accessories cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Spare Parts and Car Decoration Materials cttx, cttx Stationery cttx, cttx Textile, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx