Your cart is currently empty!
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢሾፍቱ ከተማ የሚገኘው የእንስሳት ሕከምና እና ግብርና ኮሌጅ ለ2018 በጀት ዓመት የሚውሉ የዶሮ መኖዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 15, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር እ/ህ/ግ/ኮ 002/2018
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢሾፍቱ ከተማ የሚገኘው የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ለ2018 በጀት ዓመት የሚውሉ የዶሮ መኖዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም:-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው አንዲሁም በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ከታወቀ የዶሮ መኖ የምርመራ ናሙና ሰርተፍኬት መስጠት ከሚችሉ የግልም ሆነ ከመንግስት ተቋም ማቅረብ አለባቸው።
- ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ የታክስ ከፋይ (Tin No) የምስክር ወረቀት ፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ /EGP/ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 138,681.00 /አንድ መቶ ሰላሳ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ ሰማኒያ አንድ ብር/ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) /የባንክ ዋስትና ደብዳቤ ቼክ ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው የእንሰሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ግዥ ክፍል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን የያዘውን ሰነድ አንድ ቴክኒካል ኦሪጂናልና አንድ ቴክኒካል ኮፒ እና አንድ ፋይናንሽያል ኦርጅናልና አንድ ፋይናንሽያል ኮፒ በእናት ፖስታ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን 7፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኮሌጁ ግዥ ከፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ለመጫረት ያቀረቧቸውን እቃዎች ናሙና በሙሉ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ባሉት ቀናትና ሰዓት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።ጨረታው ከተዘጋ በኃላ የሚቀርቡ ናሙናዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን በ7፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ8፡00 ሰዓት በግልፅ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ የህዝብ በዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው መዝጊያ ሰዓት ታሽጎ በግልጽ ይከፈታል።
- በጨረታ መክፈቻ ቀኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይስተጓጎልም።
- ተጫራቾች ያሸነፏቸውን አቅርቦቶች በሚሰጣቸው ትዕዛዝ መሰረት በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው የእንሰሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት በማጓጓዝ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 0114338557 / 0912065391
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ
ቢሾፍቱ