የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የሸንኮራ አገዳ ገለባ (ባጋስ) ከወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ወደ መተሃራ ስኳር ፋብሪካ ለማጓጓዝ የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 15, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር MSF/LP/06/2025

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተገለፀውን የሸንኮራ አገዳ ገለባ (ባጋስ) ከወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ወደ መተሃራ ስኳር ፋብሪካ ለማጓጓዝ የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ይፈልጋል።

ጥቅል አንድ፡- የሸንኮራ አገዳ ገለባ (ባጋስ) ከወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ወደ መተሃራ ስኳር ፋብሪካ ለማጓጓዝ የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ (Bagasse Transportation) በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

1. ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን የሀገር ውስጥ ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።

2. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች ለጥቅል የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሠዓት ሜክሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ህንፃ ግዥ ቡድን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 215 የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ገዝተው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሲገዙ የንግድ ፈቃድ ይዘው መቅረብ ይኖርባችኋል።

4. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሠነድ ጋር የታደሰ የንግድ ፈቃድ የአቅራቢዎች የምዝገባ ሠርተፍኬት እና ለጨረታ ማስከበሪያ 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) የሚሆን በሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ አለባቸው።

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ (Proforma invoice) ላይ በማዘጋጀት በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እ.ኢ.አ. ጥቅምት 20 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ድረስ ሜክሲኮ ፊሊፕስ ሕንጻ ቢሮ ቁጥር 119 ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታው በዕለቱ ጥቅምት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 119 ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

7. ፋብሪካው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በስልክ ቁጥር፡- 0115-50 56 07, 0115-50 56 33 ሜክሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ሕንፃ

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *