Your cart is currently empty!
የባስኬቶ ዞን ላሰካ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በዋን ዋሺ ፕሮግራም የበጀት ድጋፍ ለወረዳው ትምህርት ጽ/ቤትና ጤና ጽ/ቤት አማካይነት 14 መፀዳጃ ቤት፤ ቆሻሻ ማቃጠያ እና መጣያ በጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 15, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የባስኬቶ ዞን ላሰካ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በዋን ዋሺ ፕሮግራም የበጀት ድጋፍ ለወረዳው ትምህርት ጽ/ቤትና ጤና ጽ/ቤት አማካይነት 1/ በሣሣ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የሴቶች መፀዳጃ ቤት ግንባታ 2/ ለሣሣ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግቢ ቆሻሻ ማቃጠያ ግንባታ 3/ በሱባ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የውሃ መስመር ዝርጋታ የጥልቅ ውሃ ቁፋሮ ግንባታ 4/ በሱባ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የሴቶች መፀዳጃ ግንባታ።
በት/ምት ሲሆን በጤና ደግሞ፡–
1) መፀዳጃ ቤት ግንባታ እና ቆሻሻ መጣያ በቁጥር 2 ሣሣ ጤና ከላ
2) መፀዳጃ ቤት ግንባታ እና ቆሻሻ መጣያ በቁጥር 2 ባዮ ቦረዛ
3) መፀዳጃ ቤት ግንባታ እና ቆሻሻ መጣያ በቁጥር 2 ገዘ አይማ
4) መፀዳጃ ቤት ግንባታ እና ቆሻሻ መጣያ በቁጥር 2 ኦብጫ ከተማ
5) መፀዳጃ ቤት ግንባታ እና ቆሻሻ መጣያ በቁጥር 2 ጋርባያ
በድምሩ 14 መፀዳጃ ቤት፤ ቆሻሻ ማቃጠያ እና መጣያ በጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል። በዚህም መሰረት የጨረታ ሰነድ ውስጥ በተጠቀሱት እስፔስፊኬሽን መሠረት ለማስገንባት ስለሚፈልግ የመወዳደሪያ ሃሳብ እንዲያቀርቡ ይጋበዛሉ። መ/ቤታችን ግዥውን የሚፈፀመው በጥራትም ሆነ በዋጋው ብቁ መሆኑን አረጋግጦ ከመረጠው ድርጅት/ግለሰብ/ ብቻ ነው።
ተወዳዳሪዎች የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉና በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የብቃት ማረጋገጫ ወረቀት የመልካም ስራ አፈጻጸም መረጃ፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥርና ንግድ ምዝገባ ምስክ ወረቀት ያለው/ላት። ከጠቅላላ ግዥው 3% ለመንግስት ለመከፈል ፍቃደኛ የሆነ/ች/
1. የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ ከታወቀ ባንክ የተመሰከረለት በCPO ብቻ 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር)ማስያዝ የሚችል/ትችል።
2. አሸናፊው ተጫራች ጨረታውን ማሸነፉ ከተረጋገጠ የውል ማስከበሪያ 10% እና የቅድመ ክፍያ ማስከበሪያ ተመጣጣኝ የሆነ የባንከ ጋራንቲ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከባስኬቶ ዞን ላ/ዙ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤትቢሮ ቁጥር 5 በ05/02/2018 ዓ.ም እስከ 25/02/2018 ዓ.ም ድረስ በአካል እየቀረቡ ማግኘት ይችላሉ።
4. መወዳደሪያ ሃሳብ በታሸገ ኤንቨሎፕ ሆኖ ባስኬቶ ዞን ላ/ዙ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት እስከ ቀን 25/02/2018 ዓ.ም መድረስ አለበት።
5. ተጫራቾች ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 25 ቀናት የማይመለስ ለእያንዳንዱ 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማዘጋጀት ባስ/ዞን/ላስ/ዙ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መጨመር ይኖርባቸዋል።
7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ10ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 8፡30 ሰዓት በባስ/ዞ/ላ/ዙ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ይከፈታል።
8. አሸናፊ ተጫራቾች የግንባታ ስራው የደረሰበት ደረጃ በመሃንዲስ ሲረጋገጥ ከፍያ ይከፈለዋል።
9. ከደረጃ 9 ጀምሮ ያለ ተጫራቾች መወዳደሪያ ይችላሉ።
10. መ/ቤቱ ሌላ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. ተጫራቾች የሥራ ፍቃዳቸው ያልተሟላ መረጃና የዋጋ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ እንዲኖረው አይፈቀድም፡፡
12. ተጫራቾች ማህበራት ከሆነ የመንግስት ሠራተኛ አለመሆናቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ከአደራጅ መ/ቤት ማቅረብ አለባቸው።
13. ተጫራቾች ማህበራት ከሆነ አባላት የመንግሥት ሠራተኞች አለመሆናቸውን ማረጋገጫ ከአደራጅ መ/ቤት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
14. ተጫራቾች በወቅቱ ተሟልቶ አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡ ሰለማጠናቀቃቸው ከሚመለከተው ተቋም መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
15. የጨረታው ዋጋ 22 የሥራ ቀናት ፀንቶ ይቆያል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የባስኬቶ ዞን ላሰካ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት