Your cart is currently empty!
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራከሽን ኤጀንሲ ለተቋሙ ስራ አገልግሎት የሚውሉ የእስቴሸነሪ፣ አላቂ የጽዳት እቃ፣ ፈርኒቸር፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የህንፃ መሳሪያዎችን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 15, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራከሽን ኤጀንሲ ለተቋሙ ስራ አገልግሎት የሚውሉ የእስቴሸነሪ፣ አላቂ የጽዳት እቃ ፈርኒቸር፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የህንፃ መሳሪያዎችን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር እንዲችሉ ተጋብዘዋል፡
ስለሆነም ፡–
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN ያላቸው፣
3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ/ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
5. የሚገዛው የእስቴሽነሪ እና የህንፃ መሳሪያ እቃዎች ግዥ በሎት (በጥቅል) ሲሆን ሌሎች ግዥዎች በነጠላ ዋጋ ውድድር የሚደረግ ሲሆን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥን በተመለከተ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በማለት ለየብቻ በተለያዪ ፓስታ በማድረግ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
6 የእስቴሽነሪ፣ የህንፃ መሳሪያዎች፣ የአላቂ የጽዳት እቃ፣ የፈርኒቸር እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ዓይነት ዝርዝር መግለጫ /Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ስም በተከፈተ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013197966 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ በመያዝ ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ05/02/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 20/02/2018 ዓ.ም ማግኘት ይቻላል፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በተቋሙ ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ስም በተከፈተ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000012858586 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ ኦርጅናል ከፋይናንሻል ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ አድርገው ማስያዝ አለባቸው፡፡
9. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማለትም ዋና እና ኮፒ (Original and Copy) በማለት በተለያየ ፖስታ በአንድ ኤንቨሎፕ በጥንቃቄ በማሸግ በኤጀንሲው ግዥ ኢፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት /በአየር ላይ ከዋለበት/ ቀን ከ05/02/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ቀን 20/02/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤጀንሲው ዋና መ/ቤት አደራሽ ወይም ግዥኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 03 በ20/02/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን 8፡30 ይከፈታል፣
11. የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
12. ኤጀንሲዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
13. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 222 1100 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 322 05155/058 222 110 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
14. ተጫራቾች በእያንዳንዱ የዋጋ መሙያ ገፅ ላይ ፊርማና መህተም ማድረግ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም በዋጋ መሙያው ላይ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ
ባህር ዳር