የጅማ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በ2018 የበጀት ዓመት ለተማሪዎች ምገባ የሚውል የምግብ ግብዓቶች እና የማገዶ እንጨትና የፅዳት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 15, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጅማ መምህራን /ኮሌጅ 2018 የበጀት ዓመት ለተማሪዎች ምገባ የሚውል ንጹህ ጤፍ፣ ንጹህ ሩዝ፣ አተር ክክ፣ የተቆላ የሽሮ አተር፣ ንፁህ ምስር ክክ፣ ንፁህ የስንዴ ቅንጬ፣ አንደኛ ደረጃ የዳቦ ፉርኖ ዱቄት፣ የቲማቲም ስልስ፣ ድንች፣ ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ማጅማከስ፣ የሻይ ቅጠል፣ ስኳር፣ የጎመን ዘር፣ እርሾ ኤግልስ፣ የምግብ ዘይት፣ የማገዶ እንጨትና የፅዳት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ የንግድ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

በዚህም መሠረት አንድ ድርጅት በጨረታው መሳተፍ የሚፈ መስፈርቶች፡

1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው፣ የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት፣ የቫት ምስክር ወረቀት እና የአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበት ምስክር ወረቀት ኦሪጅናልና ኮፒውን ጎን ለጎን ማቅረብ የሚችሉ።

2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ጥቅምት 5 ቀን 2018 . እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2018 . 21 ተከተታይ የሥራ ቀናት ለጨረታ የተዘጋጁ የጨረታ ሰነዶችን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በኦሮሚያ የህብረት ሥራ ባንክ በጅማ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 1000064416026 ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ከጅማ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 15 (ግዥ፣ ዕቅድ፣ ፋይናንስ አስተዳደር እና ሀብት ዳይሬክቶሬት ክፍል ) መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2% በባንክ የተመሰከረ ሲፒኦ (CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. የጨረታ ሣጥን መክፈቻ ቀንና ሰዓት አስመልክቶ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት የሥራ ቀናት ውስጥ በማስገባት 21ኛው የሥራ ቀን ጥቅምት 25 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት እስከ 400 ሰዓት ተጠናቆ በማስገባት 430 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል።

5. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃ ጅማ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ድረስ ማቅረብ አለበት።

6. ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

7. ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09-11-74-8607 / 0913-75-13-78 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የጅማ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *