በሀዲያ ዞን የሆሳዕና ከተማ አስ/ር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ከሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሠረት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች (ለመኖሪያ እና ለንግድ) የተዘጋጀ ቦታን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 17, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታው ዙር፡– 1

1. የጨረታ ዓይነት መደበኛ

2. በሀዲያ ዞን የሆሳዕና ከተማ አስ/ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት /ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ከሀ እስከ በተዘረዘረው መሠረት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች (ለመኖሪያ እና ለንግድ) የተዘጋጀ ቦታን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300 ብር በመክፈል ከማዘጋጃ ቤቱ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ዘርፍ ቢሮ ቁጥር 3 እስከ ቀኑ 1100 ሰዓት ብቻ መግዛት የሚቻል መሆኑን እናስታውቃለን፡፡ ለመደበኛ ጨረታ 10ኛው ቀን የጨረታ ሰነድ የሚሸጠው እስከ 900 ሰዓት ብቻ ነው።

3. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/ አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ ይሆናል።

4. የጨረታው ሳጥን የሚታሸገው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት 10ኛው ቀን ከቀኑ 1100 ሰዓት ይሆናል።

5. ቦታውን መጎብኘት ለሚፈልግ ተጫራች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለጸው መርሐ ግብር መሠረት የምናስጎበኝ ይሆናል።

6. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት 11ኛው ቀን ከቀኑ 430 ሰዓት በሆሳዕና ከተማ አቢዮ ኤርሳሞ ስታዲየም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡ 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።

7. ስለ ጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታው ሰነድ ማግኘት ይቻላል።

8. ማዘጋጃ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9. ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ዌብ ሳይት www.hosannaca.gov.et ማግኘት ይቻላል

ተጨማሪ መረጃ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ደውሎ ማግኘት ይቻላል።

046-555-3645

046-555-2355

046-555-2310

የሆሳዕና ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገ/ቶች /ቤት /ሆሳዕና/


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *