Your cart is currently empty!
በቂርቆስ ክ/ከ/አስ/በዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት የግዥ ቡድን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለስፖርት ምክር ቤት ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የስፖርት ትጥቅ ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 17, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡– 01/2018
በቂርቆስ ክ/ከ/አስ/በዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት የግዥ ቡድን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለስፖርት ምክር ቤት ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የትጥቅ ግዥዎችን ከዚህ በታች የተጠቀሱ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 የ ስፖርት ትጥቅ ግዥ፣
በመሆኑም ተጫራቾች፡
1. በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ የስራ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር/tin no/የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
2. የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
3. ለሚወዳደሩባቸው ሎት አይነቶች የጨረታ ማስከበሪያ ከጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሰውን በሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
4. የጨረታው ሰነድ አቀራረብ 1 ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናል፣ 1 ቴክኒካል ሰነድ ኮፒ፣ 1 ፋይናንሺያል ሰነድ ኦሪጅናል እና የፋይናንሺያል ኮፒ ለየብቻ እንዲሁም 1 ሲፒኦ ለብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. የጨረታ ሰነዱን እስጢፋኖስ ላይ በሚገኘው የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ግዥ ቡድን ቢሮ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
6. የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመቁጠር 11ኛው ቀን ላይ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በተመሳሳይ ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ ጨረታው ይከፈታል፡፡
7. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ላይ እንደ ማሳሰቢያ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– እስጢፋኖስ ከሚገኘው ከማሪዎት ሆቴል ፊት ለፊት የቂርቆስ ክ/ከ/አሰ/ 9ኛ ፎቅ፣
ስልክ፡– 011-554-8264 / 011-869-4366
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት