አጼ ቴዎድሮስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2018 ዓ.ም. አገልግሎት ላይ የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 17, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- 001/2018ዓ.ም

አጼ ቴዎድሮስ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የ2018 ዓ.ም አገልግሎት ላይ የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

ማለትም፡-

  • ሎት 1 የደንብ ልብስ
  • ሎት 2 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
  • ሎት 3 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች
  • ሎት 4 አላቂ የፅዳት ዕቃዎች
  • ሎት 5 አላቂ የሕክምና እቃዎች
  • ሎት 6 ልዩ ልዩ መሣሪያዎች
  • ሎት 7 ቋሚ እቃዎች

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል በዚሁ መሠረት ተጫራቾች፡-

  1. በመንግስት ዕቃ አቅራቢነት ተመዝግበው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች በዘርፉ ወይም በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው።
  3. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  5. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በት/ቤቱ ግዥ ንብረት አስተዳደር ከቢሮ ቁጥር 03 ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልጽ በመሙላት በመጨረሻ ቦታ ላይ ስም፣ ፊርማና ሕጋዊ ማህተም በማኖር በታሸገ ኢንቨሎፕ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2፡30- 11፡00 ዋጋቸውን በመሙላት በተጠቀሰው የስራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
  7. ጨረታው ሲከፈት የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ የሚመለስ በየሎቱ ብር 2% በcpo ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  8. ጨረታውን አሸናፊ ሆነው ከተገኙ በኋላ 10% ባሸነፉበት ዕቃ መጠን የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  9. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ እንደሚሆኑና የጨረታ ማስከበሪያው Cpo ይወረስበታል።
  10. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በተዘጋ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 በተቋሙ ጽ/ቤት ይከፈታል።
  11. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አቃቂ ንግድ ባንክ በስተጀርባ

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114 34 02 41 ደውሎ መረዳት ይቻላል

የአፄ ቴዎድሮስ የመ/ደ/ት/ቤት