የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ በ2018 ዓ.ም. በመደበኛ በጀት ለአንደኛ ደረጃ የትምህርት ቤቶች የምግብ አቅርቦት አግልግሎት የሚውል ምግብ ዱቄት ፋፋ እንዲሁም ትራንስፖርትን ጨምሮ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ለማጓጓዝ ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 17, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ በ2018 ዓ.ም. በመደበኛ በጀት ለአንደኛ ደረጃ የትምህርት ቤቶች የምግብ አቅርቦት አግልግሎት የሚውል ምግብ ዱቄት ፋፋ እንዲሁም ትራንስፖርትን ጨምሮ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ለማጓጓዝ ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

  1. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው።
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  3. በሚሳተፉበት አቅርቦት ጨረታ ክፍል አግባብ ካለው የመንግስት መ/ቤት ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ የአገልግሎት አቅርቦት እንደሚሰጡ የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣባት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ሠመራ ትም/ቢሮ ቁጥር 5 የጨረታውን ሰነድ በመግዛት የሚወዳደሩበትን ሀሳብ እና ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል እና ፋይናሻል ሰነዶችን በመለየት በ2 ኮፒ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርበቻዋል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ትምህርት ቢሮ የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በትምህርት ቢሮ የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ዳሬ/ዳሬ ቢሮ ቁጥር 5 በ16ኛው የስራ ቀን በ3፡00 ሠዓት ይከፈታል።
  9. ለአሸናፊው ተጫራች የሚከፋል ቅድሚያ ክፍያ አይኖርም፤ በመሆኑም አቅርቦቱን በተገቢ ሁኔታ በስፔስፊኬሽን መሠረት አቅርቦቱን ማቅረቡ ሲረጋጥ 100% ክፍያ ወዲያው ይፈጸምለታል።
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የስራ ሂደት ክፍል ቢሮ ቁጥር 5 በስልክ ቁጥር 033-666-01-26/033666-01:23 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

አፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *