Your cart is currently empty!
የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ቢሮ የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የመኪና መለዋወጫ እቃዎችና ጐማ ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 17, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ቢሮ የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የመኪና መለዋወጫ እቃዎችና ጐማ ህጋዊ የሆኑ አቅራቢዎች ለመግዛት ይፈልጋል።
በግልጽ ጨረታ ማሰራትና እቃዎች መግዛት ስለተፈለገ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችና ቢሮው ያዘጋጀውን የጨረታ ዶክመንት መስፈርት ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
በዚህ ግልጽ ጨረታ የሚወዳደር አቅራቢ ድርጅት በ2018ዓ.ም በጀት ዓመት የታደሰ ንግድ ፍቃድ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለበት።
1. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ሀሳብ ኦርጅናሉ አንድ ፖስታ ሁለት ኮፒዎቹን ኮፒ አንድ እና ሁለት በተናጠል በፖስታ በማሸግ የተጫራቾች ስምና ፊርማ በግልጽ ተጽፎባቸው ሶስቱም ፖስታዎች በአንድ ፖስታ ተደርጐ በሰም ታሽጐ መቅረብ ሲኖርበት የመኪና መለዋወጫ እቃዎችና ጐማ ግዥ ለሚጫረቱ እቃዎች ግዥ ዓይነቱና መጠኑ ስእላዊ መግለጫ የሚያስፈልገው ስለሆነ በከለር የታተመ ስእላዊ መግለጫ በፖስታ ውስጥ ተደርጐ በተወሰነ ጊዜና ሰዓት በአፋር ብ/ክ/መንግስት ከተማ ልማት ኮንስትራከሽን ቢሮ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 2 ለዚሁ ተብሎ የተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው
2. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ሀሳብ ቢሮው ለመግዛት የፈለገውን የመኪና መለዋወጫ እቃዎችና ጐማ ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡት መጫረቻ ሰነድ እያንዳንዳቸው 1/አንድ/ኦርጅናልና 2/ኮፒ/ ሰነድ ማምጣት ግዴታ አለባቸው።
3. የሚገዙ የመኪና መለዋወጫና ጐማ ግዥ ዝርዝር መግለጫ/specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
4. ማንኛውም የጨረታ ተወዳዳሪ ለሚያቀርባቸው እቃዎች ዋጋ 1 ፕርሰንት የጨረታ ማስረከቢያ ቢድ ቦንድ ቼክ ወይም/ CPO / ከመወዳደሪያ ሀሳብ ማቅረቢያ ጋር በፖስታ ታሽጐ በሰም ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለበት።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 1000.00 /አንድ ሺ ብር/ ከፍለው ከከተማ ልማት ኮንስትራክሽን በግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 2 መውስድ ይችላሉ።
6. የተዘጋጀው የጨረታ ዝርዝር ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ለተከታታይ /15/ ቀናት ዶክመንት ሽያጭ የሚያደርግ ሲሆን 16ኛ ቀን እስከ ጠዋት 3፡30 ጀምሮ በዛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ በማስገባት ተጫራቾች ባለቤት ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አ/ብ/ክ/መንግስት በከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ቢሮ በግዥና ፋይ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 2/1/ ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ጨረታው የሚገባና የሚከፈት ይሆናል።
7. ተጫራቾች ሰነዱን ገዝተው በመሙላትና በማዘጋጀት ኦርጂናል የመወዳደሪያ ሀሳብ ዶክመንታችሁን በአንድ ፖስታ ውስጥ በሰም በማሸግ ኮፒዎቹን በሌላ ፖስታ ውስጥ በተናጠል በሰም በማሸግ በማስገባት ሶስቱኑም ፖስታዎች በአንድ ፖስታ አድርጐ በሰም አሽገው ለዚሁ ግዥ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
8. ቢሮው ሊገዛው ያቀረበው የእቃ ዝርዝር ተጫራቾች በከለር የታተመ ስእላዊ መግለጫ ማቅረብ እቃዎቹ ቢሮ ንብረት ክፍል አምጥቶ ገቢ ማድረግ አለባቸው።
9. ሻጭ ንብረቱን በንብረት ክፍል ድረስ ወስዶ ካስረከበ በኋላ በስሙ ሞዴል 19 አስቆርጦ ሂሳብ ክፍል ወስዶ ሂሳቡን ማወራረድ አለበት።
10. የጨረታ መክፈቻ ፕሮግራሙ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ቢቀር የጨረታው መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም።
11. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገዎት በስልክ ቁጥር 033-666-00-03 /05 እና በኢሜል afarudcb@gmail.com ደውለው ይጠይቁ።
በአፋር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ
ሠመራ