በሰሜን ወሎ ዞን የራያ ቆቦ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት የጽህፈት መሳሪያ፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የመኪና ጎማና ባትሪ እና የእንስሳት መድሃኒት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 18, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን የራያ ቆቦ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር /ቤት 2018 በጀት ዓመት ለሴከተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ 

  • 1 የጽህፈት መሳሪያ፣
  • 2 ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣
  • 3 የጽዳት እቃዎች
  •  4 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
  • 5 የመኪና መለዋወጫ፣
  • 6 የመኪና ጎማና ባትሪ፣
  • 7 የእንስሳት መድሃኒት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

ስለሆነም

  • በዘርፉ የታደሰ ፈቃድ ያለው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ያለው፤
  • ውድድሩ ብር 200,000.00 ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነና የተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት፤
  • የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርና የቫት ተመዝጋቢነት የምስከር ወረቀት ከጨረታ ሰነድ ጋር አብሮ መያያዝ አለበት፤
  • የዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይቻላል፤
  • የጨረታ ሰነዱ ራያ ቆቦ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ዋና /ቤት ቢሮ ቁጥር 25 በመቅረብ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ብር 500 አምስት መቶ ብር ብቻ መግዛት ይቻላል፤
  • ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒአ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /unconditional bid bond/ ብቻ በመ/ቤቱ ግቢ በማድረግ ደረሰኙን ፖስታው ውስጥ አሽጎ አያይዞ/ ማቅረብ ይኖርበታል፤
  • የጨረታ ሰነዱን ኦርጂናል ኮፒ በማድረግ በሁለት በተለያየ ፖስታ በማዘጋጀት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርበታል፤
  • አሸናፊው ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5/አምስት/ ተከታታይ ቀናት የውል ማስከበሪያ ይዞ በመቅረብ ውል መውሰድ አለበት ካልቀረበ የጨረታ ማስከበሪያው 1% ለመንግስት ገቢ ይሆናል፤
  • በአሸናፊው ተጫራች ላይ ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት አይቻልም፤
  • የጨረታ መዝጊያ ከተጠናቀ በኋላ ባቀረቡት መወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፤
  • አሸናፊው ማሸነፉ ተገልጾለት በአምስት ቀናት ውስጥ ውል ወስዶ ወደ ስራ መግባት አለበት፤
  • ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ድረስ ሰነዱን ራያ ቆቦ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር /ቤት ቢሮ ቁጥር 25 የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 500.00/አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መውሰድ ይቻላል
  • ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን 400 ታሽጎ በዚሁ ቀን 430 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
  • የጨረታ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ እንዳይኖረው በጥንቃቄ መሞላት አለበት፤
  • ጨረታው የሚከፈተው ቅዳሜና እሁድ ወይም መንግስት ካላንደር የሚዘጋው ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን
  • መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
  • ለበለጠ መረጃ በመስሪያ ቤቱ የስልክ ቁጥር 0333341014 0912356697 ወይም 0910977530 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል

የራያ ቆቦ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር /ቤት