Your cart is currently empty!
የለደግ ሚድዋይፈሪ ኮሌጅ የተለያዩ እቃዎች ግዥ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 18, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ (NCB 001/2018)
የለደግ ሚድዋይፈሪ ኮሌጅ የተለያዩ እቃዎች ግዥ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ።
1. ተጭራቶች በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊና የዘመኑ ግብር ከፍለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ በመንግስት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የተመዘገቡበት የአቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት መለያቁጥር (ቲን) ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የግብር ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስራ አራት ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ስድስት ኪሎ ከመርሃ ዕውራን ማህበር ዝቅ ብሎ ከበላይ ዘለቀ ትምህርት ቤት ፈለፊት በሚገኘው ለደግ ሚድዋይፈሪ ኮሌጅ የበጐ አድራጐት ድርጅት ዲን ኦፊስ ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ መሠረት በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ በለደግ ሚድዋይፈሪ ኮሌጅ የበጐ አድራጐት ድርጅት ስም ሞልተው ከአሪጅናል የመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
|
ተ.ቁ |
የግዥው ዓይነት |
የጨረታው መለያ ቁጥር |
የጨረታ ማስከበሪያ (በብር) |
የጨረታው መዝጊያ |
የጨረታው መከፈቻ |
||
|
ቀን |
ሰዓት |
ቀን |
ሰዓት |
||||
|
1 |
ቋሚ እቃዎች ሎት 1 |
NCB 001/2018 |
3,000.00 |
በ15ኛው ቀን |
4.30 |
በ15ኛው ቀን |
4.45 |
|
2 |
የጽሕፈት መሣሪያዎች ሎት 2 |
NCB 001/2018 |
3,000.00 |
በ15ኛው ቀን |
4.30 |
በ15ኛው ቀን |
4.45 |
|
3 |
የጽዳት አገልግሎት እቃዎች ሎት 3 |
NCB 001/2018 |
3,000.00 |
በ15ኛው ቀን |
4.30 |
በ15ኛው ቀን |
4.45 |
|
4 |
ጥራጥሬና ሸቀጣሸቀጦች ሎት 4 |
NCB 001/2018 |
3,000.00 |
በ15ኛው ቀን |
4.30 |
በ15ኛው ቀን |
4.45 |
|
5 |
የጤና መጠበቂያ |
NCB 001/2018 |
3,000.00 |
በ15ኛው ቀን |
4.30 |
በ15ኛው ቀን |
4.45 |
1. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የመወዳደሪያ ሰነዶች ቴክኒካል አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሺያል አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ ለየብቻው አሽገው የጨረታውን ስምና ቁጥር በመፃፍ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ተከታታይ ቀን ጀምሮ በሰንጠረዡ መሠረት በኮሌጁ ዲን ኦፊስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኃላ የሚመጡ ተጫራቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
2. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ስድስት ኪሎ ከመርሃ ዕውራን ማህበር ዝቅ ብሎ በበላይ ዘለቀ ትምህርት ቤት ፊለፊት በሚገኘው ለደግ ሚድዋይፈሪ ኮሌጅ የበጐ አድራጐት ድርጅት ዲን ኦፊስ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግስት የሥራ ቀን ካልሆነ ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።
3. ተጫራቾች የጨረታዉን ዝርዝር ሁኔታዎች ከጨረታ ሰነዱ ላይ የሚያገኙ ሲሆን ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 0955-11-11-11 ደውለው ወይም በአካል መጠየቅ ይችላሉ። ሌጁ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የለደግ ሚድዋይፈሪ ኮሌጅ የበጎ አድራጎት ድርጅት