የመቱ ካርል ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ2018 ዓ.ም በጀት ለህሙማን የሚውል የምግብ አቅርቦት፣ የተለያዩ የህትመት አገልግሎት እና የጭነት አገልግሎትን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 18, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የጨረታ ማስታወቂያ

የመቱ ካርል ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ2018 ዓ.ም በጀት ለህሙማን የሚውል የምግብ አቅርቦት፣ የተለያዩ የህትመት አገልግሎት እና የጭነት አገልግሎትን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ከዚህ በታች የተገለጹ መስፈርቶችን የሚያሟሉ በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

1. ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው፤

2. ቫት/ ቲኦቲ ተመዝጋቢ መሆኑን ተለይቶ መገለጽ አለበት፣

3. ተወዳዳሪ በሌሎች ተጫራቾች ላይ ተመስርቶ ዋጋ ማቅረብ እና መወዳደር የተከለከለ ነው።

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመግዛት እና ይህ ማስታወቂያ በአስር ተከታታይ የስራ ቀናት በመሙላት በታሸገ ፖስታ የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ የጨረታው ሰነድ በማስገባት ተወዳዳሪዎች በተገኙበት በ9፡00 ሰዓት ጨረታው የሚከፈት ይሆናል።

6. መ/ቤቱ የተሻለ ነገር ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ 09 17 34 42 32
በኦሮሚያ ጤና ቢሮ የመቱ ካርስ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል