የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኅብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ የ2018 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የጽሕፈት መሳሪያ፣ የጽዳት ዕቃ፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የተሽከርካሪዎችን ጥገና እና ፈርኒቸር ዕቃዎችን ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾች አወዳድሮ ውል በማስገባት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 18, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

መጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኅብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ 2018 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የጽሕፈት መሳሪያ፣ የጽዳት ዕቃ፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የተሽከርካሪዎችን ጥገና እና ፈርኒቸር ዕቃዎችን ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾች አወዳድሮ ውል በማስገባት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

ዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈ ተጫራቾች፡

1. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው፣

3. በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበና መረጃ ማቅረብ የሚችል

4. እያንዳንዱ ተጫራች የተዘጋጀውን ጨረታ በዓይነት እና ሰነድ በመግዛት ዘወትር በሥራ ሰዓት የመ/ቤቱ ግዥ ፋይ//አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 20 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፣

5. ለኤሌክትሮኒክስ፣ ለጽ/መሳሪያ፣ የጽዳት ዕቃዎች እና የፈርኒቸር ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል የጨረታ ሰነድና የፋይናሽያል ሰነዱን ለብቻ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለእያንዳንዱ ተመሳሳይ አንድ አንድ ኮፒዎችን አዘጋጅቶ በኤንቨሎፑ የውስጥ ገፅ ዋናና ኦርጅናል ወይም ኮፒ ብሎ በመፃፍ አሽገው ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤

6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት ሲሆን 15ኛው ቀን ከቀኑ 800 በፊት ብቻ ይሆናል፡፡ ጨረታው 15 ቀን ከቀኑ 800 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 09:00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የግዥ ፋይ//አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ በግልፅ ይከፈታል፡፡ ሆኖም 15 ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፍተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይሆናል፡፡

7.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO 2% ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣

8. ጨረታውን በከፊል መጫረት የሚፈልግ ተጫራች ከተዘረዘሩት የዕቃ ዓይነቶች አንድ ወይም ከአንድ በላይ መርጦ መጫረት ይችላል፣

9. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ/ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ የሚፈልጉ ከሆነ በስልክ ቁጥር 046 212 6892 ዘወትር በሥራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ፣

10. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

የመ/ቤቱ አድራሻ፡የቀድሞ የደ////// ግብርና ቢሮ 1 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 20

የሲዳማ ክልል ኅብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ

ሐዋሳ