Your cart is currently empty!
በድሬዳዋ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ፑል እና በስሩ ላሉት ተቋማት ለ2018 በጀት ዓመት ለስራ የሚያገለግሉ የፅዳት እቃ ግዥ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 19, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በድሬዳዋ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ፑል እና በስሩ ላሉት ተቋማት ለ2018 በጀት ዓመት ለስራ የሚያገለግሉ የፅዳት እቃ ግዥ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡
ጨረታውን መወዳደር ለሚፈልጉ ተሳታፊዎች የጨረታ መስፈርት
1. በዘርፉ የተሰማሩ የንግድ ፈቃድ ያለው
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ
3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TON NO) ያለው
4. የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
5. የአቅራቢነት ሠርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
6. የጨረታ ማስከበሪያ 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) ወይም CPO ወይም በጥሬ ማስያዝ ይኖርበታል
7. ተጫራቾች የሚጫረቱባቸው ሠነድ ዋጋ በመሙላት በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ22ኛው ቀን በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 300.00 ብር (ሶስት መቶ ብር) ከተማ ስራ አስኪያጅ ፋይናንስ ግ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል መግዛት ይችላሉ።
9. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችሁ በተገኙበት 4፡30 ሰዓት በከተማ ስራ አስኪያጅ ፋይናንስ ግ/ን/አስ/ዳይሬከቶሬት ከፍል ይከፈታል።
10. መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሠነድ ላይ በአቅራቢነት መሞላት ያለበት ተሞልቶ የተጫራች ፊርማና ማህተም ከሌለው ተቀባይነት አይኖረውም።
11. የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ኦርጅናል እና ኮፒ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት፡፡
ማሳሰቢያ፡ መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ
በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ የስ/ ቁ. 09 27 80 34 67 ወይም 09 15 75 53 24
አድራሻ፡– ድሬዳዋ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ቢሮ (ቴሌ ትራፊክ መብራት አጠገብ)
ድሬዳዋ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት