ኤልሳቢ አነስተኛ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ተሽከርካሪ ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Reporter(Oct 19, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

ኤልሳቢ አነስተኛ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና በሰንጠረዡ የተመለከተውን ተሽከርካሪ በአዋጅ ቁጥር 216/92 እና 1147/2019 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ንብረቱ ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

የተበዳሪው ስም

 

የንብረት አስያዥ ስም

 

አበዳሪው ቅርንጫፍ

 

የተሸከርካሪው

የሐራጅ መነሻ ዋጋ(ብር)

ሐራጁ የሚከናወንበት ቀንና ሰዓት

 

ዐይነት

 

የሞተር ቁጥር

የሻንሲ ቁጥር

የተሠራበት ዘመን

ታርጋ(ሰሌዳ) ቁጥር

/ሚካኤል አባተ ያዘው

 

ተበዳሪው

 

አዲሱ ገበያ

 

አውቶሞቢል

 

LF479Q3* 080500001

 

LLV2A2A10  ‘80034590

 

2010

 

.3-B64063

 

ብር 249,874.74 (ሁለት መቶ አርባ ዘጠኝ ስምንት መቶ ሰባ አራት ብር 74/100 ሳንቲም)

ጥቅምት 25 ቀን 2018 .ከጠዋቱ 400 እስከ ጠዋቱ 530 ስዓት

 

የጨረታ ደንቦች

1. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከተቋሙ በማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በካሽ በመክፈል ከተቋሙ ዋና ቢሮ ቀርቦ መውሰድ ይችላል።

2. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ የብር መጠን 1/4 (አንድ አራተኛ) በተረጋገጠ የባንክ የክፍያ ማዘዣ/ሲ.ፒ.ኦ/ በኤልሳቢ አነስተኛ ፋይናንስ ተቋም ኢማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።

3. ሐራጁ የሚከናወነው አዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ጃክሮስ አካባቢ ወደ ጎሮ መታጠፊያ 100 ሜትር ገባ ብሎ ብርሃን ባንክ ያለበት ሕንፃ ጎን የሚገኘው የተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ነዉ።

4. የንግድ ማህበራትን ወክሎ ለመጫረት የማህበራቱን መመስረቻ እና መተዳደርያ ደንብ የያዘና በማህበራቱ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ስነድ በማቅረብ ይሆናል።

5. ተበዳሪው (መያዣ ሰጨው) በሃራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገርግን ባይገኙም ሃራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።

6. ንብረቱን ለመጎበኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ፕሮግራም በማስያዝ በስራ ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ በመገኘት መጎብኘት ይችላሉ።

7. የጨረታ አሸናፊዉ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው ገንዘብ ለተቋሙ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

8. ለጨረታ የቀረበውን ተሸከርካሪ አሸንፎ የገዛ ተጫራች ከገዛው ተሽከርካሪ ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈል ማንኛውንም ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ከስም ዝውውር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጭዎች ይከፍላል።

9. ተሽከርካሪውን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ / ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን(ተሽከርካሪውን) ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ተቋሙ ኃላፊነት አይወስድም። ገዢው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል።

10. ተቋሙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 666 75793/ 011 673 2829 ይደውሉ።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *