Your cart is currently empty!
የአማራ ብሔ/ክ/መ/የሰ/ሸ/ዞን የመ/ጌ/ም/ወ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ለተለያዩ ሥራ ሂደቶች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 19, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ብሔ/ክ/መ/የሰ/ሸ/ዞን የመ/ጌ/ም/ወ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ለተለያዩ ሥራ ሂደቶች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች ባለው ዝርዝር መሰረት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- ሎት 1፡– የጽ/መሳሪያ
- ሎት 2፡– ሌሎች አላቂ የጽዳት እቃዎች
- ሎት 3፡– የኤሌክትሮኒክስ ቋሚና አላቂ እቃዎች
- ሎት 4፡– ቋሚ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 5፡– ልዩ ልዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎች
- ሎት 6፡– የተለያዩ ህትመቶች
- ሎት 7፡– የተሰፋ /የተዘጋጁ አልባሳት እና ጫማዎች ብትን
1. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ከጥቅምት 10/07/2018 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 25/2/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ብቻ ሲሆን ጨረታው በዚሁ እለት ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ ወዲያውኑ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
2. በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ ቲን ነምበር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. በሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ላይ የጨረታ መዝጊያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ራሳቸውን ከጨረታ ማግለል አይችም።
4. ተጫራቾች የሞሉበትን ዋጋ በማስላት ቫትን ጨምሮ የጨረታ ማስከበሪያ 1% ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ያስያዙትን ደረሰኝ ፎቶ ኮፒ አድረገው ማቅረብ አለባቸው። የ/ሲፒኦ ከሆነ ኦርጅናሉ መቅረብ አለበት።
5. በጨረታ ሰነዱ ላይ የሞሉትን ዋጋ ከተፈላጊ መረጃዎች ጋር በማያያዝ ኮፒና ኦርጅናሉን በሁለት ፖስታ በማሸግ ኦርጅናሉን የያዘውን ፖስታ ላይ ኦርጅናል ኮፒውን ፖስታ ላይ ኮፒ ተብሎ መፃፍ ይኖርበታል።
6. በተጨማሪም የንግድ ፈቃድና የመሳሰሉት መረጃዎች ከኦርጅናል ዶክሜንት ጋር ተያይዘው መቅረብ አለባቸው።
7. በሁለቱ ፖስታዎች ላይና እንዲሁም በጨረታ ዋጋ መሙሊያ የጨረታ ሰነድ ላይ የተጫራቾች ስም፡– ፊርማና ማህተም ሊኖረው ይገባል እንዲሁም ስርዝ ድልዝ እንዳይኖረው ካለውም በፍሉድና ሌሎች ማጥፊያ ሳይጠቀሙ አንድ ስረዝ ብቻ በመጠቀም ፖራፍ በማድረግ መሙላት ይኖርባቸዋል።
8. በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
9. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፅላቸው ከ5 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ በፍ/ቤታችን በመገኘት ከሎት 1- እስከ ሎት 7 ላሉት የውል ማስከበሪያ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝና ውል መፈፅም አለባቸው፤ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርበው ውል ካልፈፅሙ በግዥ መመሪያው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያውን በመውረስ ለመንግስት ገቢ ያደረጋል።
10. ተጫራቾች በጨረታ አፈፃፀም ሂደት ላይ ቅሬታ ካላቸው በግዥ አዋጅና መመሪያው መሰረት አሸናፊነትና ተሸናፊነት በተገለጸ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ።
11. ለተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ብር ከአሸናፊ ተጫራች ጋር ውል እንደተፈፀመ ተመላሽ ይደረጋል።
12. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን ሁሉንም ተጫራቹ መሙላት አለበት። ሁሉንም እቃዎች ካልሞሉ ከውድድሩ ውጭ ሊደረጉ ይችላሉ።
13. ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት የኅዝብ በዓላት ፣ ቅዳሜና እሁድ ከዋለ በቀጣይ የሥራ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
14. የጨረታ ሰነዱን በመጌ/ም/ወ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን በቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በመምጣት በማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዋ/ገ/ያዥ በመግዛት መወድ ይችላሉ።
15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ከሎት ı እስከ ሎት 7 አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ወይም በተናጥል ፍ/ቤቱ በሚያዋጣው መልኩ ሲሆን በጥቅል ከሆነ በድምር ነው።
16. ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈልጉ በስልክ ቁጥር፡– 0116850005/116850101 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
በሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የመ/ጌ/ም/ወ/ፍ/ቤት