Your cart is currently empty!
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ለ2018 ዓ.ም ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 19, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ለ2018 ዓ.ም ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በግልጽ ጨረታ ቁጥር 03/2018
- ሎት 1፡- የመኪና ጌጣጌጥ እቃዎችና የተለያዩ የመኪና ጎማዎች
- ሎት 2፦ የጽህፈት መሳሪያዎች ፣
- ሎት 3፡- የጽዳት ዕቃዎች ፣
- ሎት 4፡-የደንብ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (ቲን ነምበር)፣ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት፤ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በጨረታ መሳተፍ ስለመቻላችሁ የሚገልጽ ማስረጃ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባችሁ፤
ማስታወቂያው አየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ሆኖ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፤ ናሙና ማቅረብ ግዴታ ነው፡፡
ተጫራቾች የቴክኒክና የዋጋ ፖስታቸውን ለይተው ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የቴክኒክ ፖስታው ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችና የጨረታ ማስከበሪያ መያዝ ያለበት ሆኖ በጨረታ መክፈቻ ወቅት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የጨረታ ሰነዱን ከአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ከመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 507 ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 8፡00 ሰዓት በማይመለስ ብር 600 (ስድስት መቶ ብር) በመግዛት መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት አንድ 30,000.00(ሰላሳ ሺህ) ፣ ሎት ሁለት ብር 5.000(አምስት ሺህ) ፣ሎት ሶስት ብር 4,000.00(አራት ሺህ)፣ ሎት አራት ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ) CPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ
የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ አድራሻ፡- መገናኛ ስሪ ኤም ሞል ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 507 ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011- 639-46-55/ 011-639 30–10 መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ