Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተለያዩ ንብረቶች በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Reporter(Oct 19, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጰያ ንግድ ባንክ ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተገለፁትን እና በእዳ ማካካሻነት የተረከባቸውን የተለያዩ ንብረቶች በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
ለጨረታ የቀረበው ሕንፃ/ንብረት አገልግሎት
|
ቤቱ/ ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የቦታው ስፋት ካ.ሜ |
የካርታው /የባለቤትነት ማረጋገጫ ሠነድ |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
የሚሽጥበት ሁኔታ |
||
|
ከተማ |
ወረዳ |
ቀበሌ |
||||||
|
1 |
መኖሪያ ቤት |
ሑመራ |
ሰቲት |
1 |
320 |
ሑ/ማ/8060/አ-845/85 |
5,598,011.56 |
በዝግ ጨረታ |
|
2 |
መኖሪያ ቤት |
ሑመራ |
ሰቲት |
4 |
500 |
ሑ/ማ/9916/አ-845/85 |
4,616,464.44 |
» |
|
3 |
መኖሪያ ቤት |
ሑመራ |
ሰቲት |
2 |
400 |
ሑ/ማ/9194/አ–ባ-2/85 |
961,896.80 |
» |
|
4 |
መኖሪያ ቤት |
ሑመራ |
ሰቲት |
2 |
870 |
ሑ/ማ/9778/አ-845/85 |
6,823,036.70 |
» |
|
5 |
መኖሪያ ቤት |
ሑመራ |
ሰቲት |
1 |
1,576.5 |
ሑ/ማ/130291/አ-845/85 |
4,600,711.93 |
» |
|
6 |
ንግድ ቤት |
ሑመራ |
ሰቲት |
4 |
300 |
ሑ/ማ/9779/አ-845/85 |
5,426,954.19 |
» |
|
7 |
ትምህረት ቤት |
መተማ ዮሃንስ |
መተማ ዮሃንስ |
1 |
4500 |
ኢን-011 |
13,775,152.31 |
» |
ማሳሰቢያ
1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00/ ሶስት መቶ/ በመክፈል ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሑመራ፣ጃንተከል ቅርንጫፍ እንዲሁም ጎንደር ዲስትሪክት ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ።
2. ማንኛውም ተጫራች ሌሎች ተጫራቾች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም።
3. ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋውን 25%/ሃያ አምስት በመቶ/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ/CPO/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስም በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. በጨረታው አሸናፊ ሆኖ ለሚቀርብ ተጫራች ባንኩ ባለው የብድር ፖሊሲና መመሪያ መሠረት ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
5. በተራ.ቁ 1፣2፣3፣4 እና 5 ከተጠቀሱት መኖሪያ ቤቶች በስተቀር በተ.ቁ 6 እና 7 ላይ ያሉት የንግድ ቤት እና ት/ቤት በሽያጭ ገንዘብ ላይ የሚታሰብ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ገዢ ጨምሮ ይከፍላል።
6. ተጫራቾች ለንብረቶች የሚሰጡት ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ካሰፈሩ በኋላ የጨረታ ማስከበሪያና ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶችን በፖስታ በማሸግ ህዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ጎንደር ዲስትሪክት ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ አስመዝግበው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. ጨረታው ህዳር 16 ቀን 2018 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ከላይ በተራ ቁጥር ስድስት ላይ በተገለፁት አድራሻዎች ይከፈታል።
8. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 18 02 60 97 ጃንተከል ቅርንጫፍ፣ 09 62 56 77 11 ሑመራ ቅርንጫፍ፣ 058 111 4979 ጎንደር ዲስትሪክት እና 09 36 57 26 51 ባንኩ በእዳ የተረከባቸው ንብረቶች አስተዳደር በመደወል ወይም ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ጎንደር ዲስትሪክት ጽ/ቤት በአካል ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል።
9. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ