Your cart is currently empty!
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 04 ጨፌ ጤና ጣቢያ የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 21, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር ለሚ ኩ/ከ/ከ/
ጨፌ ጤ/ጣ 03/2018 ዓ.ም
የጨረታ ቁጥር 01/2018
የሚገዛው ዕቃ ተዛማጅ አገልግሎት:-
- ሎት 1 ቋሚ /ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 3 አላቂ የጽዳት እቃዎች
- ሎት 4 ፈርኒቸር
- ሎት 5 ህትመት ሥራዎች
- ሎት 6 ልዩ ልዩ ጥገናዎች
- ሎት 7 የተለያዩ ህክምና መገልገያ መሳሪያዎችና
- ሎት 8 የሰራተኛ ደንብ ልብስ
ከዚህ በላይ የተገለጸውን ሥራ ላይ መወዳደር የምትፈልጉ አቅራቢዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያሳደሱ ተጨማሪ እሴት ታክስ/የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ በስተመጨረሻ ተመላሽ የሚሆን ከዚህ በላይ ለተገለጹት ሎቶች ለሚወዳደሩበት ሎት በመለየት/ ለሎት 1. 20,000.00 /ሀያ ሺህ ብር/ ለሎት 2. 10,000.00/ አስር ሺህ ብር ለሎት 3. 10.000.00/አስር ሺህ ብር / ለሎት 4 20,000 ሀያ ሺ ሎት 5. 10,000 (አስር ሽህ ብር ሎት 6. 5,000 አምስት ሺህ ሎት 7. 20,000 ሀያ ሺህ. ሎት 8. 10,000 አስር ሺህ ብር ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን በመለየት ፖስታው ላይ በመግለጽ ዋናውን ፎቶ ኮፒ በማድረግ የገዙትን ዋናውን የጨረታ ሰነድ እና ፎቶ ኮፒውን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በጤና ጣቢያው ግዥ ክፍል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- በጥቃቅን እና አነስተኛ ለተደራጁ ማህበራት ካደራጃቸው አካል ለሚያመርቱበት ሥራዎች ከበላይ ኃላፊ ተፈርሞ ለጨረታ ማስከበሪያ እና ለውል ማስረከቢያ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚያው ቀን 5፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጤና ጣቢያው ባዘጋጀው ቢሮ ይከፈታል።
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑትን ላሸነፋበት የውል ማስከበሪያ 1ዐ% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/ቼክ ማቅረብ አለባቸው።
- የተሰረዘ፣ የተደለዘና ግልጽነት የሌለው የጨረታ ሠነድ ይሰረዛል።
- ጤና ጣቢያው መ/ቤቱ/ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋጋ ስትሞሉ ከነቫት ጨምራችሁ መሙላት አለባችሁ።
- አድራሻ፡- በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ጨፌ ጤና ጣቢያ ከውሀ ታንከር ትንሽ አለፍ ብሎ ባለው ማዞሪያ ላይ በመውረድ ወደ ውስጥ አስፓልቱን 200ሜ ገባ ብሎ የመጨረሻው አርባ ስልሳ ፊት ለፊት እንገኛለን።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፟፦ 09 02 34 04 53 / 09 17 70 58 11 /09 04 95 58 01 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 04 ጨፌ ጤና ጣቢያ
cttx Advertising and Promotion cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx Furniture cttx, cttx Health Care, cttx Health Related Services and Materials cttx, cttx House and Building cttx, cttx House Furniture cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Machinery cttx, cttx Maintenance and Repair cttx, cttx Medical Equipment and Supplies cttx, cttx Office Furniture cttx, cttx Office Machines and Accessories cttx, cttx Office Machines and Computers cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Others cttx, cttx Printed Advertising Materials cttx, cttx Printing and Publishing cttx, cttx Promotional Items cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Stationery cttx, cttx Textile, cttx Vehicle (garage service) cttx, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx, Medical Industry cttx