በቢሾፍቱ ከተማ የጨለለቃ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በ2018 የበጀት ዓመት የጨለለቃ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ ለቢሮ ውስጥ የተለያዩ የጽሕፈት መሣሪያዎችን፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ቋሚና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስና ፈርኒቸሮች፣ የተለያዩ የመኪና ጎማ፣ የደንብ ልብስ እና የተለያዩ የህትመት ሥራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 21, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

በቢሾፍቱ ከተማ የጨለለቃ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በ2018 የበጀት ዓመት የጨለለቃ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ ለቢሮ ውስጥ የተለያዩ የጽሕፈት መሣሪያዎችን፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ቋሚና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ኤሌክትሮኒክስና ፈርኒቸሮች፣ የተለያዩ የመኪና ጎማ፣ የደንብ ልብስ እና የተለያዩ የህትመት ሥራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተገለጸውን መመሪያ በመከተል ከዚህ ጋር ተያይዞ በቀረበው -ገጽ እስፔስፊኬሽን መሠረት ተጫራቾች ይህንን ጨረታ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል።

  1. ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል በዘርፉ የተሰማሩ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና ያሳደሱ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች ከ100,000.00 ብር በላይ ለሆነ ግዥ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  3. በገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር ወይም በሌላ በሚመለከታቸው ፈቃድ ሰጪ አካላት አቅራቢዎች ዝርዝር ተርታ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  4. በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ከሆኑ ከገቢዎች ወይም ከጉምሩክ በየሦስት ወር የተጨማሪ እሴት ታክስ መክፈላቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
  5. ማንኛውም ተጫራቾች በጨረታው ተካፈይ ለመሆን ተመላሽ የሚሆን ካቀረበው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ከሕጋዊ ባንክ የተረጋገጠ /CPO/ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከ2፡30-11፡30 ሰዓት የማይመለስ ብር 150.00 (አንድ መቶ ሀምሳ ብር ብቻ) በመከፈል በጨለለቃ ክፍለ ከተማ ገ/ኢ/ ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች በጨረታ በሰነዶቻቸው ላይ አድራሻውን ስልክ፣ ፖስታ፣ ኢ-ሜል፣ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በትክክል መግለጽ ይኖርባቸዋል።
  8. መ/ቤቱ ካቀረበው እስፔስፊኬሽን ወይም መስፈርት /Standard/ በታች ማቅረብ አይቻልም። ሰነዱን መሰረዝ መደለዝ አይቻልም።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዋና እና ኮፒ በሰም በታሸገ በተለያዩ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  10. አሸናፊ ተጫራቾች ወይም ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት ጨለለቃ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት መጋዘን ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት።
  11. ማንኛውም ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቼዋለሁ ማለት አይቻልም።
  12. ጨረታው የሚቆየው ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ይሆናል። በነጋታው በ15ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻችሁ የማይገኙ ከሆነ ጨረታው የሚከፈት ይሆናል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  13. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  14. በተጨማሪም ሙሉውን መመሪያ ከሚገዙት ሰነድ ጋር ስላለ ሰነዱን ሲገዙ የሚያገኙ ይሆናል።
  • አድራሻ፡- ቢሾፍቱ ከተማ ኦዳ ነቤ ሆቴል ፊት ለፊት 100 ሜትር ገባ ብሎ ማግኘት ይቻላል።
  • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0114342001/0923008007 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በቢሾፍቱ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጨለለቃ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት