በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን ማረሚያ ተቋም በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በሃገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ አወዳድር ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 21, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን ማረሚያ ተቋም 2018 በጀት ዓመት በመንግሥት ከተበጀተልን መደበኛ በጀት ላይ ለተቋሙ የሚያገለግል በተለያዩ በአምስት ዓይነት ሎቶች የተገለጹትን ዝርዝር በአንድ ዓመት የሚቆይ ከዚህ በታች በሎት1 /አንድ/አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎችና ዕቃዎች፣ በሎት 2 /ሁለት/ – የጽዳት ዕቃዎች፣ በሎት 3 /ሦስት/ – የደንብ ልብስ፣ በሎት 4 /አራት/ – የቢሮ ፈርኒቸሮችን፣ በሎት 5 /አምስት/ – የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በተዘረዘሩት መሠረት በሃገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ አወዳድር ለመግዛት ይፈልጋል።

1. ሎት አንድ (1) – አላቂ የጽሕፈት መሳሪያዎችና ዕቃዎች፣

2. ሎት ሁለት (2) – የጽዳት ዕቃዎች፣

1 ሎት ሶስት (3) – የደንብ ልብስ፣

4 ሎት አራት (4) – የቢሮ ፈርኒቸሮች፣

5 ሎት አምስት (5) – የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣

በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተቀመጡትን የመጫረቻ መስፈርቶችን ማሟላት አለባችሁ፡፡

1. ሎት 1 – አላቂ የጽሕፍት መሳሪያዎችና ዕቃዎች ጨረታ 15,000.00 CPO ሎት 2 – የፅዳት ዕቃዎች 5,000 CPO ሎት 3 – የደንብ ልብስ 5,000 CPO ሎት 4 – የቢሮ ፈርኒቸሮች 20,000 CPO ሎት 5 – የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 20,000 CPO ማቅረብ የሚጠበቅባችሁ ሲሆን ሰነዱን ከጨረታ ጋር በማሸግ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡

2. በዘርፉ የተመዘገቡ ሕጋዊና የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማቅረብ የሚችሉ፤

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN Number) ማቅረብ የሚችሉ፤

4. የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤

5. የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም TOT ተመዝጋቢ የሆኑ፤

6. ከክፍያው 3% ተቀናሽ ለመክፈል ፈቃደኛ የሆኑ፤

7. ማንኛውም ተወዳዳሪ ጨረታውን አወዳድሮ ሲያሸንፍ የግዥውን ጠቅላላ ዋጋ ቢያንስ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡

8. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በሚዛን ማረሚያ ተቋም በመቅረብ ከፋይናንስ ክፍል ቢሮ የማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ ብቻ በመግዛት የምትጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት ኦሪጅናልና ኮፒ በመለየት በሁለት ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

9. ከሎት አንድ እስከ አምስት ባሉት ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ለሚጫረቱበት ጨረታ ናሙና ይዘው /አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

10. የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን 11/02/2018 . እስከ 25/02/2018 . ጀምሮ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በቀን 26/02/2018 . 800 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ 830 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሚዛን ማረሚያ ተቋም ፋይናንስ ቢሮ /ስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በመጀመሪያ የሥራ ቀን ወይም ሰኞ የሚከፈት ይሆናል፡፡

11. ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ማሸነፉ በተገለፀለት 5 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ተቋሙ በሚያዘጋጀው ውል በመግዛት ያሸነፈውን ጨረታ እስከ ተቋሙ ድረስ አምጥቶ የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡

ማሳሰቢያ፡

  • ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • ጨረታው ክፍት ሆኖ የሚቆየው ከቀን 11/02/2018 . እስከ 25/02/2018 . ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በቀን 26/02/2018 . ነው።
  • ማንኛውም ተጫራቾች በጨረታው ላይ በሚሳተፉበት ወቅት ከላይ በቀረበው መስፈርት መሠረት የጨረታ ማስያዢያ /CPO/ ማቅረብ አለባቸው፡፡

ሚዛን ማረሚያ ተቋም