በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰሜን ሸዋ ዞን ደብረብርሃን ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ለፍርድ ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ልዩ ልዩ ህትመቶች፣ ቋሚ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ልዩ ልዩ እቃዎች፣ የቢሮ እቃዎች እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማስጠገን ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 22, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 04/2018

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰሜን ሸዋ ዞን ደ/ብርሃን ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ለፍ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ

1. አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች

2. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች

3. ልዩ ልዩ ህትመቶች

4. ቋሚ እቃዎች

5. የጽዳት እቃዎች

6. ልዩ ልዩ እቃዎች

7. የቢሮ እቃዎች እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና 

በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማስጠገን ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር / TIN / ያላቸው

4. የግዥው መጠን ብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ/VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1 – 4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

6. የዕቃዎቹን አይነት ዝርዝር መግለጫ እስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ።

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከፍ/ቤቱ የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 20 ከተራ ቁጥር 1- 4 ለተዘረዘሩት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ከተራ ቁጥር 5 – 7 ለተዘረዘሩት የማይመለስ ብር 50 / ሃምሣ ብር / በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

8. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ ጠቅላላ ዋጋውን ቫቱን ጨምሮ 1% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ / በመ/ቤቱ ሕጋዊ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው።

9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት በደ/ብርሃን ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢቁጥር 20 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።

10. ጨረታው በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጐ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል።

11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ ደ/ብ/ከ/ወ/ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 20 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥራችን 011 681 61 85 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።

የደብረ ብረሃን ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት