በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የገላን ጤና ጣቢያ የ2018 ዓ.ም ቋሚ እቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የሠራተኛ የደንብ ልብሶች እና ተዛማጅ እቃዎች፣ የተለያዩ የህትመት ውጤቶች፣ የተለያዩ አላቂ የፅዳት እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2018

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የገላን ጤና ጣቢያ የ2018 ዓ.ም ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚሁ መሠረት መ/ቤቱ አወዳድሮ መግዛት የሚፈልጋቸው እቃዎች

  • ሎት 1 ቋሚ እቃዎች 80,000 ሺህ
  • ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች 30,000 ሺህ
  • ሎት 3 የሠራተኛ የደንብ ልብሶች እና ተዛማጅ እቃዎች 30,000 ሺህ
  • ሎት 4 የተለያዩ የኅትመት ውጤቶች 20,000 ሺህ
  • ሎት 5 የተለያዩ አላቂ የፅዳት እቃዎች 57,000 ሺህ

ሲሆኑ የሚከተሉት መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

  1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የዘመኑ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው ሆኖ የቲን ቫት ተመዝጋቢ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. የግዥ መጠን 50,000(ሃምሳ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት።
  3. የሚገዙ እቃዎች እና ዝርዝር መግለጫ (እስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) ከፍለው ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃዎች በዝርዝሩ መሠረት የጨረታ ሰነዱ መሠረት በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒውን በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ቢሮቁጥር 55 በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. የጨረታ ማስከበሪያ 2% በየሎቱ በብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. የጨረታ ሳጥን በአስራ አንደኛው ቀን (11) የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው ቀን ላይ በሥራ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 4፡30 ላይ በጤና ጣቢያው የስብሰባ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 56 ይከፈታል
  8. ስርዝ ድልዝ ካለ ፓራፍ መደረግ አለበት።
  9. ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት የማያግድ መሆኑን እንገልፃለን።
  10. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. ጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች በሀገር ውስጥ ምርት ላይ የተሳተፉ መሆኑን በቂ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቶታል ዝቅ ብሎ ወደ አዳማ በሚወስደው መንገድ ላይ በሰላም ሕንፃ ገላን ሳይት ኮንዶሚኒየም በሚወስደው መንገድ 3000 ሜ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011 435 9040

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የገላን ጤና ጣቢያ