በደቡብ ወሎ መስተዳደር ዞን የመቅደላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የሕንፃ መሣሪያዎች፣ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የቤትና የቢሮ እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ግንአ/002/2018

በደቡብ ወሎ መስተዳደር ዞን የመቅደላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ላሉ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ

  • ሎት 1 የሕንፃ መሣሪያዎች
  • ሎት 2 የጽሕፈት መሣሪያዎች
  • ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
  • ሎት 4. የቤትና የቢሮ እቃዎች
  • ሎት 5 የፅዳት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ ተጫራቾች ለጨረታ ሲመጡ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።

  1.  በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
  2.  የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው
  3. ከ200’000/ሁለት መቶ ሺህ ብር /በላይ የነጠላ ወይም የጥቅል ግዥ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለበት።
  4.  ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል የመቅደላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ማግኘት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩባቸው ሎቶች የዕቃውን ጠቅላላ ግምታዊ ዋጋ ለሎት 1. 50,000 /ሃምሳ ሽህ ብር/፣ ለሎት 2, 40,000/ አርባ ሽህ ብር/ ለሎት 3, 20,000 / ሃያ ሺህ ብር/፣ ለሎት4. 10,000 /አስር ሽህ ብር/፣ ለሎት5. 5000 /አምስት ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመቅደላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ን/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በ16ኛው ቀን ከረፋዱ እስከ 3፡30 ሰዓት ድረስ በማስገባት ይታሸጋል። በዚሁ እለት ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ በቅደም ተከተል በሥራ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ን/አስ/ደ/ ቡድን ክፍል በቢሮ ቁጥር 05 ይከፈታል። 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀናት ታሽጎ ይከፈታል።
  7. በጨረታው ለመጫረት የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 033-450-0222 በመደወል ወይም በፋክስ ቁጥር 033 450 0013 በመላክ ማግኘት ይቻላል።
  8. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ከመከፈቱ አይስተጓጎልም
  9. ጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
  10. ውድድሩ የሚካሄደው ከ ሎት 1 እስከ ሎት 5 በየምድቡ በሎት ነው።
  11. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የመቅደላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት