Your cart is currently empty!
የቤኬ ቅድመ 1ኛ እና አንደኛ ደ/ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 21, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተደዳር በለሚ ኩራ ከ/ከተማ በወረዳ 06 ት/ጽ/ቤት የቤኬ ቅድመ 1ኛ እና አንደኛ ደ/ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ማለትም
- ሎት 1፣ የትምህርት እቃዎች፣
- ሎት 2, የቢሮ እቃዎች፣
- ሎት 3, የጽዳት እቃዎች፣
- ሎት 4, የደንብ ልብስ፣
- ሎት 5, ፈርኒቸሮች፣
- ሎት 6, ፕላንት ማሽነሪዎች፣
- ሎት 7,ህትመት ስራዎች እና
- ሎት 8, ልዩ ልዩ መሳሪያዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡ –
- ለተጠቀሱት እቃዎች በዘርፉ የንግድ ስራ ላይ የተሳመሩ መሆን አለባቸው፤
- በዘመነ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር ስለመከፍላቸው ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን ሰርተፍኬት/ ያላቸው።
- በድህረ ገጽ በአቅራቢዎች በተዘጋጀው ክፍል /AGP/ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
1. ማንኛውም ተጫራች ከላይ የተዘረዘሩትን ሰነዶች ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በመለየት ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በፖስታ በማሸግ ማስገባት አለባቸው።
ተጫራቹ ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ በየሎቱ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ከኦርጅናል የጨረታ ሰነዱ ጋር ታሽጎ ማቅረብ አለበት።
|
ሎት 1 ለትምህርት እቃዎች |
15,000 ብር |
ሎት 5, ለፈርኒቸሮች |
25,000 ብር |
|
ሎት 2, ለቢሮ እቃዎች |
15,000 ብር |
ሎት 6, ለፕላንት ማሸነሪዎች |
25,000 ብር |
|
ሎት 3, ለጽዳት እቃዎች |
15,000 ብር |
ሎት 7, ለህትመት ስራዎች |
10,000 ብር |
|
ሎት 4, ለደንብ ልብስ |
20,000 ብር |
ሎት 8, ለልዩ ልዩ መሳሪያዎች |
20,000 ብር |
ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት ከት/ቤቱ ፋይናንስ ግዥ ክፍል በየሎቱ የማይመለስ 200(ሁለት መቶ ብር) ከፍሎ በመግዛት የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰነዱ ላይ በግልፅ በመሙላት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ኮፒና ኦርጅናል ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ማስገባት አለባቸው።
1.2 ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ ሎት 8 መጫረት ወይም መርጠው አንዱን ወይም ሁለቱን መጫረት ይችላሉ፡፡ ነገርግን ከእያንዳንዱ ሎት እቃዎች መራርጠው ለተወሰኑት እቃዎች ብቻ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም።
1.3 የጨረታው ሳጥን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ከፍት ሆኖ በ11ኛው ቀን በ3፡30 (ሶስት ሰዓት ተኩል) ታሽጎ በእለቱ በ4፡00 (አራት ሰዓት) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቹ /ህጋዊ ወኪል/ ያለመገኘት የጨረታ አከፋፈት ላይ ተጽኖ አይኖረውም።
1.4 የጨረታ አሸናፊ ላሸነፈው እቃ 10 ፐርሰንት ውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል።
1.5 ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
1.6 በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች በትራንስፖርት በማጓጓዝ የመስሪያ ቤቱ ንብረት ከፍል ድረስ በማስገባት ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
1.7 በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች የሚያቀርቡት እቃ በናሙናው መሰረት ካልሆነ ተቀባይነት የለውም።
1.8 በዋጋ መሙያ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይነት የለውም።
1. ቤኬ ቅድመ 1ኛ እና አንደኛ ደ/ት/ቤት በግልጽ ጨረታ የተለያዩ የጽዳት ዕቃ፣ የትምህርት እቃዎች፣የቢሮ እቃዎች፣ ደንብ ልብስ፣ ፕላንት ማሽነሪ ፈርኒቸሮችና የላብራቶሪ ግብዓቶች የህከምና እቃዎች፣ ህትመት እና ልዩ ልዩ መሳሪያዎችን በሠንጠረዥ በቀረበው መሰረት የምትጫረቱበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ ሞልታችሁ በማስገባት እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
1.1 ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የት/ቤቱ አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ቦሌ አራብሳ ልዩ ስሙ ከሰፈራ አደባባይ ወደ ባታ ማርያም በሚወስደው መንገድ ሳይት አምስት ኮንዶሚንየም መሀል መሆኑን እንገልፃለን።
በለሚ ኩራ ክ/ከተማ በወረዳ 06 ት/ጽ/ቤት የቤኬ ቅድመ 1ኛ እና አንደኛ ደ/ት/ቤት