የአራት ኪሎ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል የሰራተኞች የደንብ ልብስ፣ የስፖርት ትጥቅና እቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያ እና የፅዳት እቃዎች መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 21, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 02/2018 ዓ.ም

የአራት ኪሎ ስፖርት፣ ትምህርትና ስልጠና ማዕከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሰራተኞች የደንብ ልብስ፣ የስፖርት ትጥቅና እቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያ፣ የፅዳት እቃዎች መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን መሟላት አለባቸው፡፡

1. ለመጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ የአቅራቢ ምዝገባ ወረቀት የግብር ከፋይነት ተመዝጋቢ የቫት ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።

2. ስለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር መግለጫ በደንብ ማጥናትና ማንበብ ዋጋ ሲሞላ ከሚደርሰው ስህተት ያድናል፡፡ መስሪያ ቤቱ በሰጠው የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር ላይ የአንዱ ዋጋ መሞላት አለበት።

3. የዋጋ ማቅረቢያ ሲሞላ ስርዝ ድልዝ እንዲኖር አይፈለግም።

4 ተጫራቾች በሙሉ ሆነ በከፊል ጨረታውን ተወዳድረው ካሸነፉ በኋላ ያሸነፉበትን ዕቃ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ለማቅረብ ፈቃደኛ ካልሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል ለሚመለከተው አካልም በደብዳቤ ይገልፃል።

5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫት የተጨመረበት /ያካተተ/ መሆን አለበት።

6. የጨረታ ሰነድ ላይ ተጫራች ወይም የህጋዊ ወኪሉ ስም እና ፊርማ ማህተም ያረፈበት መሆን አለበት።

7. ተጫራቾች በሚያቀርቧቸው የጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱ ሙሉ ስም፣ አድራሻ ከፍለ ከተማ የቤት ቁጥርና የስልክ ቁጥራቸው መገለፅ አለበት፡፡

8. ተጫራቾች በሚያቀርቧቸው የጨረታ ሰነድ ከአራት ኪሎ ስፖ/ትም/ስል ማዕከል የፋይ ግዥ ንብ/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 በመምጣት የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር / በመክፈል መግዛት ይቻላል።

9. ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 /አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን፣ ጨረታውን በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ላይ የሚያበቃና ሳጥኑም ታሽጎ በማግስቱ የስራ ቀን ከሆነ ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ጨረታው የሚከፈት ሲሆን የስራ ቀናት ካልሆነ ደግሞ በቀጣዩ የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በማዕከሉ አዳራሽ ቁጥር 10 በግልፅ የሚከፈት ይሆናል።

10. ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ አስር የስራ ቀናት ውስጥ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናልና ኮፒ አድርጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ፋይ/ግዥ/ንብ/ አስተ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 ሰነዱን ማስገባት ይኖርባችኋል።

11. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ሰነድ ለማስገባት ሲመጡ የሚደራደሩበትን የዕቃ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

12. ጨረታው በግልፅ ከተከፈተ በኋላ ማንኛውንም መረጃ ዶክመንት/ አንቀበልም።

13. ለአሸናፊዎቹ ክፍያ የሚፈጸመው የተጠየቀውን ዕቃ በተጠየቀውና ባሸነፈው ናሙና መሰረት ሙሉ በሙሉ ገቢ ከተደረገ በኋላ መሆኑን እናሳውቃለን።

14. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

15. ተጫራቾች መ/ቤቱ ባወጣው የጨረታ ስነድ ላይ የእቃዎችን ዋጋ በማስፈር የማቅረብ እና የድርጅቱ ማህተም ማድረግ ይጠበቅበታል።

16. አሸናፊው ድርጅት / ከመስሪያ ቤቱ ጋር ላሸነፉት ዕቃ ለማቅረብ የውል ስምምነት ይፈርማል።

17. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ የትራንስፖርት አገልግሎት መ/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡

18. ተጫራቾች  ለሚወዳደሩበት ዕቃ CPO ብር 10,000/አስር ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

አድራሻ ፡- 4 ኪሎ ስፖርትና ትምህርት ማዕከል ቢሮ ቁጥር 7 ከስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አጠገብ ለበለጠ መረጃ ስልክ 01 11 26 1365

የአራት ኪሎ ስፖርት ትምህርትና
ስልጠና ማዕከል


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *