የዋርካ ሎጅ መናፈሻ ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ


Addis Zemen(Oct 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የዋርካ ሎጅ መናፈሻ ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 01/2018

የተጫራቾች መመሪያ

  1. ተጫራቾች በመስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር አጠናቀው የከፈሉ ስለመሆናቸው እና ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች በዘርፉ ተሰማርተው የሠሩበትን የሥራ ልምድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ተደራጅተው ለሚጫረቱ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያው እና የውል ማስከበሪያው ሲፃፍ በተደራጁበት ዘርፍ ስመፃፍ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች በቀረበው ሰነድ መሰረት አሸናፊ ተለይቶ ጨረታውን ስለማሸነፉ በማስታወቂያ ይፋ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ቀናት ውስጥ ያቀረበውን ዋጋ ገቢ በማድረግ ውል ካልተዋዋለ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች ድርጅቱ በሚያወጣው የጉብኝት ፕሮግራም መሰረት ለጨረታ የቀረበ የዋርካ ሎጅ መናፈሻ ቦታው ድረስ በመሄድ ተዘዋውረው ማየት ይችላሉ።
  8. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ በመንተራስ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
  9. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ሲያቀርቡ በሰነዱ ላይ ተፈርሞበትና የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነዶች አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ በማዘጋጀት ለየብቻው በታሸገ ካኪ ፖስታ በማድረግ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  10. ከላይ የተገለፀውን መስፈርት በማሟላትይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 የጨረታው ሰነድ የሚሸጥ ሲሆን፣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 የመስክ ጉብኝት የሚደረግበት ቀን ሆኖ፣ነገር ግን በዚሁ ዕለት የጨረታ ሰነድ የሚሸጥ ይሆንና በ11ኛው ቀን ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ጠዋት 4፡00 ሰዓት የመወዳደሪያ ሰነድ ማስገባት የሚቻል ሲሆን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ሆኖም የመከፈቻ ቀን በዓል ከሆነ ወይም የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  11. ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።

ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011 154 7226 ደውለው ያነጋግሩ።

ህንፃ ቁጥር- 2 1ፎቅ ላይ

አድራሻ፡- ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 በፅዮን ሆቴል 800 ሜትር ገባ ብሎ ልዩ ስሙ አጣሪ ሰፈር ባለው የማዕከሉ ጽ/ቤት

የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *