ደቡብ ወሎ አስተዳደር ዞን የሐይቅ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 23, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአ.ብ.ክ.መ. ደቡብ ወሎ አስተዳደር ዞን የሐይቅ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2018 በጀት ዓመት፡

  • ሎት 1 የጽህፈት መሣሪዎች፣
  • ሎት 2 ልዩ ልዩ ዕቃዎች፣
  • ሎት 3 የፅዳት ዕቃዎች
  •  ሎት 4 የተለያዩ ህትመቶች፣
  • ሎት 5 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
  • ሎት 6 የስፖርት ትጥቆች፣
  • ሎት 7 የእንስሣት መድኃኒቶችና ቁሳቁሶች
  • 1 ሎት 8 የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፣
  • ሎት 9 የባጃጅ መለዋወጫ ዕቃዎች፣
  •  ሎት 10 የሞተር ሣይክል ዕቃዎች
  • ሎት 11 የመኪና ባትሪና ጎማ ዕቃዎች፣
  • ሎት 12 የጤና መድን ህትመቶች፣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

በዚህም መሠረት 1-

  1. በዘመኑ የታደሠ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው
  2. የዕቃ ወይም የአገልግሎት ግዥው መጠን ብር 200.000.00 ( ሁለት መቶ ሺህ ብር ) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆንይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው ::
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 ( ሶስት መቶ ብር ) በመክፈል ሐይቅ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አስተዳደር ቡድን አዲሱ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለጽህፈት መሣሪዎች ብር 10000.00 ለልዩ ልዩ ዕቃዎች ብር 2,000.00 ለፅዳት ዕቃዎች ብር 4,000.00፣ ለተለያዩ ህትመቶች ብር 3,25000፤ ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ብር 1.100.00፣ ለስፖርት ትጥቆች ብር 4,150.00፣ ለእንስሣት መድኃኒቶችና ቁሳቁሶች ብር 1,100.001፣ ለመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ብር 20,000.00፣ ለባጃጅ መለዋወጫ ዕቃዎች ብር 4,926.00፤ ለሞተር ሣይከል ዕቃዎች ብር 4,000.00 ለመኪና ባትሪና ጎማ ዕቃዎች ብር 9,600.00፣ ለጤና መድን ህትመቶች ብር 3,000.00 በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ ( C.P.O ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ቢድ ቦንድ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  6. የጨረታ ሰነዱን ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሐይቅ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አስተዳደር ቡድን አዲሱ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 8 ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  7. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጐ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ( ባይገኙም ይከፈታል ) ቅዳሜና ዕሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይፈፀማል ።
  8. ማንኛዉም ተጫራች ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታዉ ዉድድር ማግለል የማይችል ሲሆን፣ በጨረታ ሠነዱ የሠጠዉን ዋጋና መግለጫ መለወጥና ማሻሻል አይችልም ።
  9. አሽናፊው የሚለየው በሉት ጠቅላላ ዋጋ ነዉ።
  10. ጽ/ቤቱ እንደ በጀቱ ሁኔታ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን ሥራዎች ብዛት 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል።
  11. አሸናፊው ድርጅት የሚቀርቡትን የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችንና የጽ/መሣሪዎችን ጥራታቸዉን ጠብቆ ሐይቅ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ወጪ አጓጉዞ በማቅረብ ንብረቱን አስረክቦ እንዳጠናቀቀ ገንዘቡን ወጪ አድርጎ ይወስዳል።
  12. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033-222-01-82 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።

በደቡብ ወሎ ዞን የሐይቅ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

የግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን