Your cart is currently empty!
በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ በአርበጎና ወረዳ ያዬ ከተማ የኮብልስቶንና የጎርፍ መውረጃ ቦይ ግንባታ RM38 እና RM58 (Cooble stone Road With masonry Drainage work) ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 24, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ በአርበጎና ወረዳ ያዬ ከተማ የኮብልስቶንና የጎርፍ መውረጃ ቦይ ግንባታ በ2018 በጀት ዓመት ለማሰራት Lot RM38 እና Lot RM58 (Cooble stone Road With masonry Drainage work) ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
- ለሚሰራ የኮብልስቶንና የጎርፍ መውረጃ ቦይ ግንባታ ሥራ ደረጃቸው GC-5 እና ከዚያ በላይ ተቋራጮች 2018 በጀት ዓመት ፈቃዳቸው ያደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN NO) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ አግባብነት ካለው መንግሥት ተቋም (በፌዴራል እና በሲዳማ ክልል) የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉና የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- አስፈላጊ የግንባታ ማቴሪያሎች፣ የሥራ መሣሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶች በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መስራትና ማጠናቀቅ አለባቸው፡፡
- በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ ፕሮጀክት ሰርተው ለማስረከብ ከአሰሪና ከሚመለከታቸው መስራያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በሥራ ወቅት ከአሰሪ መ/ቤት ወይም ከአማካሪ መ/ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ኮንትራክተሮች የጨረታ ሰነድ መግዛት ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡
- በገባው ውል መሰረት ፕሮጀክት ሰርቶ ያስረከበ ተቋራጭና የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችል፡፡
- ድርጅቱ ለውድድር ያቀረበው ብቃት (ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦሪጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፡፡ ይህ ተጣርተው ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ድርጅቱ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ (bid security) የኮብልስቶንና የጎርፍ መውረጃ ቦይ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) የክፍያ ማያዣ (CPO) ብቻ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በተጫራቾች መመሪያና ደንብ መሠረት ሕጋዊ ፈቃዳቸውንና ተእታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሠርተፊኬት ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ ተጫራቾች ለሥራው የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 20 (ሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት የተለያዩ ከተማ የኮብልስቶንና የጎርፍ መውረጃ ቦይ ግንባታ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ግዥ ፋይናንስ በመክፈል ሰነዱ መውሰድ ይችላሉ።
- አንድ ተጫራች ከአንድ ሎት በላይ መወዳደርም ሆነ የጨረታ ሠነዱን መግዛት አይችልም፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታ ሳይት በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ፋይናንሺያል (ኦሪጅናል) ሁለት ሁለት ኮፒዎች እንዲሁም የቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) ሁለት ሁለት ኮፒዎች በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክሜንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ተኛው ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ግዥ ፋይናንስ አስተዳደር ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ውይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግተው ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡
- ጨረታው ላይ ባለው ጠቅላላ ዋጋ ከእስር ፐርሰንት(10%) በላይ የዋጋ ቅናሽ (Rebate) የተደረገ ከሆነ ድርጅቱ ቀጥታ ከጨረታ ወድድር ውጪ ይሆናል፡፡
- አሠሪ ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታው መግቢያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀናት ካልሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 046-212-4356
የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ